


“የመሻገር ጥሪቶች የአዲስ ብረሃን ወረቶች” በሚል መሪ ቃል በታርጫ ማዕከል የሚገኙ ተቋማት ጳጉሜ 01 የመሻገር ቀንን አክብረዋል።
በክብረ በዓሉ የተገኙ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የክልሉን ህዝብ በማስተባበር የተከናወኑ ተግባራት አኩሪ መሆኑን ገልፀዋል።
በተለይ ክልሉ ከመመስረቱ በፊት በአከባቢው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ከማጠናቀቅ ረገድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እየሰራ ያለው ተግባር የህዝብ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መልኩ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተብራርቷል።
እንደ ሀገር በበርካታ ችግሮች መሀል ለውጦች እየተመዘገቡ እንዳሉ ያብራሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበኩላቸው በክልሉ ያሉ የመልማት አቅሞችንና የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ መጠቀም የጀመሩ ለውጦችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ትርፍ ማምረትና የስራ ባህላችንን በጠንካራ በማጎልበት ገበያን መረጋጋት የሁሉም የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ ጉዳይ እንደሆነም አቶ አልማው አንስተዋል።
አልሚ ባለሀብቶችን ወደ ክልሉ በመሳቢ ለወጣቶችና ስራ አጥ ዘጎች የስራ እድል እንዲፈጠር ልሰራ እንደሚገባም ዋና አፌ ጉባኤ አንስተዋል።
ለመሻገር በትብብር መስራትና ጠንካራ የስራ ባህል ማጎልበት እንደሚገባም ተነስቷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይ በሀገር ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ እየተስተዋለ ያለውን ሰው ሰራሽ የኑሮ ወድነትንና ገበያን ለማረጋጋት በትኩረት ልሰራ ይገባል ብለዋል።
በክብረ በዓሉ በታርጫ ማዕከል የሚገኙ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
