ባለፉት ዓመታት ከተመዘገቡ ስኬቶች ልምድ በመውሰድ በመጪው ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ መረባረብ ይጠበቃል:-ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል

Spread the love

ባለፉት ብልጽግና ዓመታት ከተመዘገቡ ስኬቶች ልምድ በመውሰድ በመጪው ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ መረባረብ እንደሚጠበቅ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፕላን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል ገለጹ።

የሚዛን አማን ከተማ ብዝሃ ማዕከል የክልል ቢሮዎች የ2016 ዓ ም ጳጉሜ 1(የመሻገር ቀን) “የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች ”በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ሁኔቶች በዓሉ ተከብሯል።

ጳጉሜ 1 (የመሻገር ቀን) ቀን አስመልክቶ ለፓናል ውይይት የተዘጋጀ ሰነድ የክልሉ ፕላን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል በኩል ሰነድ ቀርበው ሀሳቢና አስተያየት ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል እንደገለጹት በክልሉ በብልጽግና ዓመታት በግብርና፣ኢንዲስትሪ በቱሪዝምና በኢኔርጅ ዘርፍ የተሻለ ለውጦች ተመዝግቧል ብለዋል።

ቀጣይ በምግብ ራስን በመቻል የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የግብርና ሴክተር ሁሉም መደገፍና ይጠበቃል ነው ያሉት።

በክልሉ እያደገ የመጣው ገቢ አሰባሰቡን ስርዓቱን የበለጠ ማሳደግ፣የቱሪዝም ዘርፍ ገቢ ለማሳደግ ዘርፉን ለቱሪስት ምቹ እንዲሆኑ የመሠረተ ልማት ችግሮችን መፍታት፣በማዕድን ዘርፍ የሚታየው ኮንትሮባንድ ንግዶችን መቆጣጠር እና መከላከል ስራዎች ቀጣይ በትኩረት እንደሚሰሩ ነው የጠቆሙት።

ኃላፊዋ የመንግሥት የመፈጸም አቅም ማሳደግ እንዲቻል በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮች በመቅረፍ ለተሻለ ህዝብ አገልግሎት አመራሩና ሲቪል ሠርቫንቱ በቁርጠኝነትና መትጋት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት።

የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቀበሌ መንገሻ በበኩላቸው እንደሀገርም ሆነ ክልል የዘንድሮ ጳጉሜ 1 (የመሻገር ቀን) ባላፉት ብልጽግና ዓመታት የተመዘገቡ ድሎችን በመዘከር የተሻገርናቸውን ፈተናዎች በማስታወስ ለቀጣይ ዓመታት ለድል በሚያነሳሳ መልኩ የሚከበር በመሆኑ ካለፉት ጊዜያት ቀኑን ለየት ያደርጋል ብለዋል።

በክልሉ ለተሪዝም፣ማዕድን፣ኢንዲስትር እና ለግብርና የሚውሉ እምቅ ሀብቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዚህም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሴክተሩን በቴክኖሎጂ ማዘመን ፣የሌማት ትሩፋት ኢንሼቲቭ ማጠናከር፣አረንጓዴ አሻራ ስራዎች ማተኮር፣ ኑሮ ውድነት በሚያባብሱ ህገወጦችን መቆጣጠር የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በብልጽግና ዓመታት የተመዘገቡ ለውጦችን በማጠናከር ለቀጣይ ለተሻለ ለውጥ በትብብር ሁሉም ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ኑሮ ውድነትን ማሸነፍ እንዲቻል በአከባቢዎች ያሉ ሰፊ የውሃ አማራጮችን በመጠቀም፣የግብርና ግብዓት ቴክኖሎጂ የአጠቃቀም በማሻሻል የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት መሰራት ይጠበቃል ብለዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *