የካፈቾ ብሔር የአዲስ ዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ) እየተከበረ ይገኛል

Spread the love

የ2017 ዓ/ም የካፈቾ ብሔር የአዲስ ዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ) በዓል በደማቅ ህዝባዊ ተሳትፎ የነገስታት መናገሻ በሆነው ‹‹ቦንጌ ሻምበቶ›› በደማቅ ባህላዊ ክዋኔዎች ታጅበው እየተከበረ ይገኛል።

የፌዴራል ፖሊሲ ማርች ባንድ ለዕለቱ ክብር እንግዶች ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

በበዓሉ ለመታደም ከሀገረ ሩስያ የተገኙ የውጭ ሀገራት ዜጎች የሀገራቸውን ባህል የሚያሳይ የባህል አልባሳትን በመልበስ በበዓሉ ታድመዋል።

የካፈቾ ባህላዊ ምክር ቤት (ምክሬቾ) አባላት እና ከሁሉም የዞኑ አከባቢዎች በዚህ ታሪካዊ በዓል ለመታደም የተገኙ የአከባቢው ተወላጆችና በየደረጃው ያሉ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች በባህል አልባሳት አሸብርቀው በዓሉን አድምቀውታል።

አጠቃላይ የበዓሉ ኩነት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲሁም በአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት እየተላለፈ ይገኛል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *