


ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ክልላዊ የጸጥታ ሁኔታን የተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
በክልሉ አሁን ላይ አንጻራዊ ሠላም መኖሩንና ይህንንም በዘላቂነት ማስቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርገዋል።
ክልሉ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰንባቸው የድንበር እንዲሁም በአርብቶ አደር አካባቢዎች የሚከሰተው የጸጥታ ችግር በዘላቂነት በሚፈታበት ሁኔታ ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር መክረዋል ።
የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ በበኩላቸው የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተም ለመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ገለጻ አድርገዋል።
በክልሉ አዋሳኝ በሆኑ አካባቢዎች የተጀመረው ጸጥታን የማረጋገጥ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በመከላከያ ሠራዊት የማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘዉዱ በላይ በክልሉ ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ ተናግረዋል በአርብቶ አደሩ አካባቢ የሚስተዋሉ ግጭቶችንና ዝርፊያዎች የሚቆሙበት ሁኔታ እንዲፈጠርም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር እንደሚሰራም ተናግረዋል ።
ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ በክልሉ ሠላምን በዘላቂነት ለማስቀጠል ከክልሉ መንግስት ጋር ተባብረው እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ከደቡብ ሱዳን አርብቶአደሮች በኩል የሚያጋጥሙ ትንኮሳዎችንና ዘረፋዎችን ለማስቆም የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢዉ በቋሚነት እንደሚሰፍር ሌቴናል ጀነራሉ ገልጸዋል።
በውይይቱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና የመከላከያ ሰራዊት የማዕከላዊ ዕዝ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል ።
