200 ሚሊየን የሕክምና ቴስት ኪቶችን በዓመት የሚያመርት የቻይና ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ላይ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

Spread the love

ጉዋንዥሁ ዎንዶ ባዮቴክ የተባለ 200 ሚሊየን የህክምና ቴስት ኪቶችን በዓመት የሚያመርት የቻይና ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ገብቶ መዋዕለ ንዋዩን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷ የጉዋንዥሁ ዎንዶ ባዮቴክ ኩባንያ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷የፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ የሚገኝ ዘርፍ መሆኑን በመግለጽ ይህም ኩባንያው በፍጥነት ወደ ስራ ገብቶ ስራ እንዲጀምር ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና የቻይናውያን ባለሃብቶች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከ40 በላይ ቻይናውን ባለሃብቶች በሙሉ አቅማቸው ስራ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው÷በዚህም ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድልን መፍጠር ችለዋል ማለታቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኩባንያው ተወካዮች በበኩላቸው÷ድርጅቱ በሁለት ምዕራፎች ስራውን እንደሚያከናውን ገልጸው በዚህም ከ15 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለማድረግ ማቀዱን ጠቁመዋል፡፡

ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባም ወደ ሌሎቸ የአፍሪካ ሀገራት ለመላክ በእቅድ መያዙ ተመላክቷል፡፡

ጉዋንዥሁ ዎንዶ ባዮቴክ ኩባንያ ከ150 በላይ ሃገራት ምርቱን የሚያቀርብ በጤና ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የሚገኝ በፈረንጆቹ 1992 የተመሰረተ የቻይና ኩባንያ ነው ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *