“ባለፉት ሶስት ወራት ከ20 የማያንሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ ተካሂደዋል”

Spread the love
  • ጠቅላይ ሚኒስተርር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

ባለፉት ሶስት ወራት ከ20 የማያንሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ተካሂደዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተርር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ባለፈው ዓመት ዓመቱን ሙሉ 20 ዓለም አቀፍ ኮንፈረሶችን አላካሄድንም፤ ዘንድሮ በሶስት ወር ብቻ 20 የሚደርሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን አካሂደናል ብለዋል፡፡

በቀጣይም በርካታ ዓለም ዓቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ ይካሔዳሉ ሲሉ አመላክተዋል፡፡

የኮሪደር ልማት እና በኢትዮጵያ የተፈጠረው አውድ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ኮንፈረንሶችን ለመሳብ እድል መፍጠሩን አንስተዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የግሉ ሴክተር ከመንግስት ጋር በመተባበር የተገነቡት የገበታ ፕሮጀክቶች ውጤት እያስገኙ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *