በዓመት እስከ 130 ሚሊዮን ተጓዦችን የሚያስተናግድ ኤርፖርት እንገነባለን፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

በአፍሪካ ግዙፍ የሚያስብለንን ትልቅ ኤርፖርት ለመገንባት ጥናት አጠናቀናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክርቤት ማብራሪያቸው ወቅት ተናግረዋል።

አሁን ያለው የቦሌ ዓለም ዓቀፍ ኤርፖርት በዓመት ከ25 ሚሊዬን ለማይበልጡ መንገደኞችን ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ይህን ለማሳደግ አዲስ ኤርፖርት መገንባት ማስፈለጉን ጠቅላይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።

በዚህም በዓመት ከ100 እስከ 130 ሚሊዮን ተጓዦችን ማስተናገድ የሚችል አዲስ ኤርፖርት ለመገንባት ጥናቱ ተጠናቋል ብለዋል።

ይህ ኤርፖርት አሁን ካለው የቦሌ ዓለም ዓቀፍ ኤርፖርት በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባ እና ሁለቱን ኤርፖርቶች በባቡር በማገናኘት በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ትዕምርት (ምልክት) የሆነው አየር መንገድ በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ትልቁ ኤርፖርትም ያለው እንዲሆን ያስችለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዳዲስ 124 ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ስለማዘዙ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአየር መንገዱን ግዝፈት ሁለንተናዊ ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።

ይህም በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ሁለተኛ የሆነውን በእጥፍ የሚበልጥ ግዙፍ አየር መንገድ እንዲሆን የሚያስችልም ጭምር ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *