


በምዕራብ ኦሞ ዞን የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት በሚል በሁለት ማዕከላት ለተከታታይ 10ቀናት የነበረው የአመራር ስልጠና ተጠናቋል።
በጀሙ ማዕከል የነበረው ስልጠና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ እንደተናገሩት በህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና አመራር በተግባር ማሳየት ይጠበቃል ብልዋል።
አመራሩ አርቆ በማሰብ እና አልቆ በመስራት እና በማየት የህዝብ ተጠቃሚነት ላይ ትኩረት ማድረግ ይጠበቃል ነው ያሉት።
በዚህም የአመራሩን አቅም በመገንባት በቀጠይ ለተሻለ ልማትና እድገት እንዲሠራ ዕድል የፈጠረ እንደሆነም ነው አቶ ጌታቸዉ የተናገሩት።
በቀጣይም የተግባር አንድነት እና የአስተሳሰብ አንድነት ላይ በንፁህ ህሊና ህዝባችንን በማገልገል በሁሉም መስክ ለውጥ ለማምጣት መትጋት እንደሚገባም አመላክተዋል።
