በምዕራብ ኦሞ ዞን በማጂ ቱም የስልጠና ማዕከል ”የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ ዕድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ 10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

Spread the love

ስልጠናው አመራሩን በአመለካከትና በተግባር አንድነት የሚገነባና የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም የሀገርን ሠላምና ብልጽግና ለማረጋገጥ አቅም የፈጠረ እንደሆነ ተገልጿል።

የምዕራብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በድሉ መዓዛ በማጠቃለያቸው፦ ስልጠናው አመራሮች ያሉበትን ቁመና እያመላከተ የዕውቀት አድማሳቸውን በማሳደግ ረገድ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል።

የተሻለ መሪ ለመሆን አመራሮች በሥነ-ምግባር እራሳቸውን ማነጽ እንደሚገባቸው የጠቀሱት አቶ በድሉ በተለይም ዕውቀታቸውን ከማሳደግ ባሻገር በአመለካከት ብልጽግና መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ተቋም መትከልና ሌብነትን መፀየፍ የሁሉም አመራር ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ የገለፁት አቶ በድሉ አንድ በሚያደርጉን ዞናዊ ገዥ ትርክቶች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረራገጥ በተሰጠን ተልዕኮ ልክ መፈፀም እንደሚገባ ጠቅሰው በተለይም የፀጥታውን ሥራ በዘላቂነት ለመፍታት በቅርበትና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በቀጣይ በሁሉም መዋቅሮች በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርትና ሌሎች ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ የስራ መመሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *