የህልም ጉልበት፣ ለእመርታዊ እድገት ” በሚል መሪ ቃል በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ላለፉት አስር ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው 3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ በስኬት ተጠናቋል።

Spread the love

በማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ለአመራሩ የሥራ መመሪያ የሰጡት የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ አካሉ እንደገለፁት የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥና የኅብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።

ህልማችንን ለማሳካት በተገቢው መተለምና የወል ትርክትን በማፅናት እንዲሁም መተግባር ከምንም ጊዜ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነውም ብለዋል።

ከስልጠናው ማግስት ጀምሮ በንድፈ ሃሳብና በመስክ ጉብኝት ያገኙትን ግንዛቤ ወደ መሬት በማውረድ የኅብረተሰቡን ህይወት ለማሻሻል በትጋት መሥራት እንደሚያስፈልግም አቶ ታሪኩ አብራርዋል።

በቀጣይ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን አመራሩ በመገንዘብ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አመራር በመሆን ለጋራ ተጠቃሚነት ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

አመራሩ እንደዞን የሚታዩ ችግሮችን በመለየትና በመፍታት በተቃራኒው ደግሞ በርካታ ዕድሎች መኖራቸውን በመረዳት በተቀናጀ ጥረት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በተገቢው መወጣት እንዳለባቸውም ተብራርቷል።

ዞኑ አሁን ላይ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ዘርፎች ላይ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው ።

ከለውጡ በፊት የዞኑ የመሠረተ ልማት ጥያቄ ሆኖ ለበርካታ ጊዜ ሲጠየቁ የነበሩ የአስፓልት መንገድ ሥራ በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኙ ቢሆንም ባለፉት አምስት አመታት ከታርጫ ወላይታ ሶዶ፣ ከታርጫ ጅማና ከታርጫ ወልዳሃኔ ዱርጊ መንገዶች ተጀምረው በመገንባት ላይ እንዳሉም አቶ ታሪኩ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *