በኮንታ እና ካፋ ዞኖች በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸው ላለፉ ዜጎች የክልሉ መንግስት የተሰማውን ልባዊ ሀዘን ይገልጻል ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት

ትናንት ምሽቱን የጣለው ከባድ ዝናብ በንብረትና በሰው ህይወት ላይ ጉዳት በማድረሱ ማዘኑን ገልጿል።

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ምሽቱን በጣለው ከባድ ዝናብ የ6 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።

በተመሳሳይ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ በደረሰዉ የመሬት ናዳ 4 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በክልላችን አሁንም ከፍተኛ የሆነ የዝናብ መጠን በመኖሩ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የክልሉ መንግስት ጥሪዉን አቅርቧል።

በዚህም ህይወታቸው ላለፉትና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ በቀጣይ ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ስራ እንደሚሰራ ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *