አመራሩ ያገኘውን ዕውቀትና ልምድ ወደተግባር በመቀየር ለህብረተሰቡ ለውጥ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

Spread the love

በኮንታ ዞን “የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተጠናቋል።

በማጠቃለያው መድረክ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ሰልጣኞች በነበራቸው ቆይታ በቂ ዕውቀትና ክህሎት ያገኙበት እንደሆነና የ3ኛ ዙር ስልጠና ካለፈው ዓመት ልምድ ተወስዶበት በተሻለ የቀረበበት እንደሆነ አስረድተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ በዓለም ደረጃ አጭር ዕድሜ ካላቸው ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱን እየለወጠና ወደ ዕድገት ጎዳም እየመራ ያለ ፓርቲ ስለመሆኑ ገልፀው ለአመራሩ፣ ለአባሉ አልፎም ለሌሎችም ዜጎች የሚጠቅሙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በስልጠናው “የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ስር የተነሱ የግብርና፣ የትምህርት፣ የጤና፣ የልማትና መሰል ጉዳዮችን ሰልጣኞች በቀጣይ መሬት ላይ በማውረድ በ10 ወራት ውስጥ የሚጠበቁ ውጤቶች በዞኑ እንዲመዘገቡ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

አሁን ወቅቱ የሩጫና የውድድር እንዲሁም የህዝቡ የመልማት ፍላጎት እየጨመረ የመጣበት በመሆኑ እንደ አመራር ያሉ ተግዳሮቶችና ሀብቶችን በመለየት ቀድመን በማቀድ መስራት ይገባል ብለዋል።

በዞኑ በየመዋቅሩ የሚገኙ አመራሮች ሀገራዊ ትርክት አስተሳሰብ በመገንባት ለተግባር ውጤታማነትና ሁሉአቀፍ ዕድገት ለማምጣት ከስልጠና የተገኙ ተሞክሮዎችና ከሌላ አከባቢ የታዩ ልምዶችን ወደ ህዝቡ በማውረድ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

በህዝቡ ውስጥ የሚታዩ ወቅታዊ የሪፎርም ጉዳዮች ሌሎች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዳያስከትል የአገ/ሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በመስራት ፓርቲው ላይ አመኔታ እንዲያሳድሩ መስራት ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አመራሩ ወደ ህዝብ ወርዶ የሚነሱ ጉዳዮችን ማዳመጥና ጥያቄዎችን መፍታት ላይ ትኩረት እንዲያደረግ አሳስበዋል።

በግብርናው ዘርፍ በመጠንና በጥራት የተሻለ ምርት እንዲመረት መስራትና መሬት ፆም እንዳያድር መትጋት እንደሚገባ አንስተው ዞኑ በሌማት ትሩፋት፣ በፍራፍሬና መሠል ዘርፎች ያለውን እምቅ አቅም በተገቢው መጠቀምና ሁሉም መዋቅሮች የሚታይ ስራ አቅደው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል ።

የአገ/ሎት አሰጣጡ ለህዝቡ በቅርበት እንዲሰጥና የፐብሊክ ሰርቫንት አገ/ሎት እንዲሻሻል ትኩረት ይሻል ያሉት አቶ ታከለ ወጣቶችን በገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ማዕከል አድርጎ በዘመናዊ መልክ ማንቀሳቀስ፣ የት/ቤቶችን ደረጃ ማሻሻልና ውጤት ማምጣት፣ ጤና ኬላዎች በሙሉ አቅም አገ/ሎት እንዲሰጡ ማድረግና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ መፈፀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ሰልጣኞች በስልናጠው ማጠቃለያ ለአንዲት አቅመ ደካማ እናት ቤት መስሪያ የሚሆን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

ፓርቲው ሰው ተኮር በመሆኑ እየተካሄዱ የሚገኙ የበጎ ፍቃድ አገ/ሎት ተግባራት ተጠናክሮ ሊመሩ እንደሚገባም ተገልጿል ሲል የዘገበው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *