የሸካ ዞንን ሰላም በማጽናት በሁሉም ዘርፎች ዉጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የሸካ ዞንን ሰላም በማጽናት በሁሉም ዘርፎች ፊት እንዲወጣና በቀጣይ 5 ዓመታት የተያዙ የልማት ዕቅዶች ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ ውይይት ተካሂዷል

የከተማ ኮሪደር ልማቶች፣የመልሶ ማልማት ፣ከተማን ለኢንቨስትመንት ማዘጋጀትና መከታተል በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይ አዳሪ ትምህርት ቤት በመክፈት ተወዳዳሪ ትዉልድ ለመፍጠርና በሌሎችም የልማት ሥራዎች ዙሪያ ምክክር ተካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማዉ ዘዉዴና የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ በማህበራዊና በኢኮኖሚ ዘርፍ የ5 ዓመት ዕቅዶች ተግባራዊነት ሁሉም ተግቶ በመስራት ለጋራ ተጠቃሚነት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

በዞኑ ያሉ ጸጋዎችንና ሌሎች በርካታ መልካም ዕድሎችን በመጠቀም የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም አመራሮች በቁርጠኝነት ሊሠሩ እንደሚገባቸዉ አሳስበዋል።

በዞኑ ሰላም እንዲሰፍን በተሰራዉ ልክ የተለያዩ የልማት ዕቅዶችን ለማሳካት ያለዉን ሀብትና የሰዉ ኃይል በማስተባበር መስራት እንደሚገባ የገለጹት የመድረኩ ተሳታፊዎች ለዚህም የሚጠበቅባቸዉን ለመወጣት እንሰራለን ማለታቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *