



መንግሥት የአገር ውስጥ ገበያ ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን ትኩረት አድርጎ እየሰራበት ካለው የብርዕ ሰብሎች አንዱ ሩዝ ነው።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም በዘንድሮው የምርት ወቅት 13 ሺህ 452 ሄክታር መሬት በሩዝ ዘር ተሸፍኗል።
በሸካ ዞን ቆይታችንም በአርሶአደሩ ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሩዝ እርሻ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን መመልከት ተችሏል።
በዞኑ በዘንድሮው መኸር 2 ሺህ የሚጠጋ መሬት በሩዝ ምርት የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ቀድመው የደረሱ የሩዝ ምርት በተሟላ መልኩ የማሰባሰብ ተግባር ተጀምሯል።
በ12 ክላስተር (ኩታ ገጠም) ከለማው ከዚሁ የሩዝ ምርት በሄክታር 40 ኩንታል ምርት ለማግኘት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በዚህ በአጠቃላይ ከ75 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።
ሩዝ በቀላል ጉልበት የተሻለ ምርት የሚገኝበት የብርዕ ሰብል አይነት በመሆኑ በአከባቢው አርሶአደሮች ተመራጭ የግብርና ስራ ነው የተገለጸው።
በዕድገቱ በዛብህ
