
አቶ ተመስገን አብዲሳ ለኮሚሽኑ በአጀንዳነት የሚቀርቡ አጀንዳዎች አጀንዳ የሚያስብላቸው መገለጫ ባህሪያቸው፣ የአጀንዳዎቹ መዳረሻቸው የት እንደሆነ፣ የአጀንዳ ባህሪያትስ ምንድናቸው?
የኮሚሽኑ የአጀንዳነት መስፈርት ምን ምንድ ናቸው ? በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለሚዲያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
አቶ ተመስገን በሰጡት ማብራሪያ በሀገር አቀፉ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በመግቢያው የተገለጸውን ጉዳይ መሠረት በማድረግ ልዩነቶች መኖራቸውንና ለምክክሩ ምክንያት መሆናቸውን አብራርተዋል።
እንደችግርም ፖለቲካዊ ፣ኢኮኖሚያዊና የጸጥታ ችግሮች በዋናነት ተጠቃሽ መሆናቸውንና እነዚህን እንደ ምክንያት በማንሳትም በአጀንዳነት ምክንያት እንደሚሆኑም አብራርተዋል ።
ኮሚሽኑ የተቋቋመው በተለያዩ አካላት የተነሱ ልዩነቶችን በተለያየ መንገድ በመለየት በማማከር ሀገራዊ መግባባትን ማምጣት ይገባል ሲሉም ገልጸዋል ።
በዚህም የተቀጠረ ስራ የምክክር ኮሚሽኑ ይሰራልም ብለዋል።
ለአጀንዳ መነሻነትም እጅግም መሠረታዊ በሆኑ በተለያዩ አካላት መካከል መለያየት መኖሩንና ያሉ ልዩነቶችን መለየቱ ደግሞ አንዱና ቀዳሚ አጀንዳ እንደሆነም አብራርተዋል ።
በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን 5 መሠረታዊ ምዕራፎች ያሉ ሲሆኑ እነዚህን ተግባር ላይ በማዋል ልዩነቶችን አጥብበን ሀገራዊ መግባባትን ማምጣት አለብን ብለዋል።
የአጀንዳ ባህሪያቶችም መሠረታዊ እና ሀገራዊ የሆኑትን አጣምሮ የሚለዩበትና የተለያየንበት መሠረታዊ ምክንያቶችንም እነዚህ ናቸው በማለት ለኮሚሽኑ የሚመጡበት እና ለአጀንዳ ቀረጻ የሚያገለግሉ መሆናቸውን አቶ ተመስገን አብራርተዋል ።
አጀንዳዎች የመጨረሻ ግባቸው በሀገራዊ ጉዳዮች የተለያየንባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ምንድናቸው የሚሉትን ኮሚሽኑ ይለያል፤ በእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ያመካክራል፤ ተሳታፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለምክክር ቀርቦ የመፍትሔ ሀሳብ ለማምጣት መሆኑንም አቶ ተመስገን አብራርተዋል ።
በታጠቅ አበበ
