








የክልል ተቋማት የቦንጋ ማዕከል የአስተዳደር ዘርፍ መሠረታዊ ድርጅት አመራሮችና አባላት ብልፅግና ፓርቲ የተመሠረተበት 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል አክብረዋል።
በክብረ በዓል አከባበር ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፈ አቶ ነጋ አበራ ለመላው ለፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች እንኳን ለፓርቲያችን 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ።
ፓርቲያችን ብልፅግና ፓርቲ ከተመሠረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም በአባሉ ፣በአመራሩ እና በህዝቡ ተሳትፎ በርካታ አንጸባራቂ ድሎችን አስመዝግቧል እያስመዘገበም ይገኛል ብለዋል።
የፓርቲያችን መርሆች ፣እሴቶች እና እሳቤዎች እንደ ሀገር እና ክልል ለጀመርነው ተስፋ ሰጪ የለውጥ ሂደት እና ለተገኘው ፈርጀ ብዙ ስኬቶች ሚናቸው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።
ፓርቲያችን ከህዝቡ ትልቅ ይሁንታ አግኝቶ የመጣ በመሆኑ ለህዝቡ የገባውን ቃል እውን ለማድረግ ከውስጥም ከውጭም ጫናዎችን ተቋቁሞ እና ተግዳሮቶች እየተፈተነ ጭምር አያሌ ስኬቶችን አስመዝግቧል።
ባለፉት ዓመታት አዳዲስ ድሎችና ስኬቶች ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፈተና ብዛት ያመለጡንን ዕድሎች ና ህልሞችን እውን እንዲሆኑ አባሉን አመራሩን ህዝቡን አቀናጂቶና አስተባብሮ በመስራት ምንዳችንን ለማብዛት ተግቶ መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
የፓርቲያችን እሳቤዎች፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትልሞቻችን አቅም መሆን የሚችሉ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ነጋ እነዚህን ህልሞቻችን በቁርጠኝነት በመተግበር ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና ማማ ላይ ለማድረስ አባሉ በየተግባሩ የመሪነት ሚናውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የፓርቲው አመራርና አባልን የአስተሳሰብና የተግባር በማጎልበት ተግዳሮቶችን በጽንአት በማለፍ የፓርቲያችን አላማና ህልሞችን ለማሳከት የተቀናጀ የጋራ ርብርብ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ለእስካሁኑ ስኬታማ ጉዞ የፓርቲው አመራር እና አባላት ተሳትፎአቸው ከፍተኛ ድርሻ መባርከታቸውን የገለጹት አቶ ነጋ አበራ ይህንን የነቃ ተሳትፎ ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል በሁሉም ዘርፍ አመርታዊ ለውጥ ለማስመዝገብ ከወትሮ በተለየ መልኩ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
