ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመታት ባከናወናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አኩሪ ድሎችን ማስመዝገብ ችሏል ፦አቶ ነጋ አበራ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ ዓመት ምስረታ በዓል አከባበር ዙሪያ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ በመግለጫቸው

ፓርቲያችን የሀሳብ ፓርቲ እንደመሆኑ መጠን የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ይገኛል ብለዋል።

አቶ ነጋ አበራ በመግለጫቸው ብልጽግና የለውጥ ፍላጎት በፈጠረው ግፊት የተወለደ በልማት ዕድገት ውስጥ የህዝቡ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ የተመሠረተ ፓርቲ መሆኑን ጠቅሰዉ ፓርቲው በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ የተረጋጋ ሰላም እንዲኖር፤ ፍትሃዊ፤ ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ዕድገት ሁሉንም ባሳተፈ መልኩ ተጠቃሚ እንዲያደርግ ከመሻት የመጣ ፓርቲ እንደሆነም ገልጸዋል።

ከለውጡ በፊት የተገኙ ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆኖ የፍትሃዊነት ችግር ያለበት በመሆኑ ይህንን በማረም የህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲቻል በጋራ ርብርብና አንድነት ተመስርቷል ብለዋል።

አቶ ነጋ አበራ ብልጽግና ፓርቲ ከተመሠረተ ወዲህ ከትናንት ያደሩ ልማቶችንና ወቅቶች የፈጠሩአቸው ፍላጎቶችን በመሻገር ዘርፈ ብዙ የልማት፤የሰላም እና የመልካም አሰሰተዳደር ጥያቄዎችን እየፈታ የመጣና እየፈታ የሚገኝ ፓርቲ እንደሆነም አብራርተዋል።

በሌላ በኩል አዳጊ ፍላጎቶችን እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረጉ ስራዎችን አልሞ በመስራት አኩሪ ስኬቶችንና ውጤቶችን ማስመዘገብ ችሏል ብለዋል ።

ፓርቲው ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብዙ ውስጣዊና ውጫዊ ጫናዎችን በመቋቋም የመጣበት ሂደት ቀላል የማይባልና በፓርቲው መሪነት የተመዘገቡ ውጤቶች ለነገ ስንቅና ተሞክሮ የሚሆኑ እንደሆነም አቶ ነጋ አንስተዋል።

የተመዘገቡት ስኬቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ከአባሉ ጋር በመገናኘት ሂደቱን እንዴት እንዳለፍን፤በሂደቱ የተገኙ ስኬቶች ምን እንደሆኑ፤ከስኬቶች መማር ያለባቸውና ቀጣይ ፓርቲውን ማጠናከር የሚያስችልባቸው ጉዳዮችን ለይተን መጓዝ እንዲቻል ሰፊ ስራዎችን መስራት ባለብን ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

በክልሉ በየደረጃው በሚገኙት የአስተዳደር እርከኞች ፓርቲው የተመሠረተበትን የአምስተኛ ዓመት አስመልክቶ የሚዘክር የተለያዩ ፕሮግራሞች የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና በሚል መርህ ሀሳብ እየተከናወኑ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

የተገኙ ስኬቶችን የበለጠ ለማስረጽ የሚገጥሙንና እየገጠሙን ያሉ ተግዳሮቶችን በጋራ እየተሻገሩ ወደ ፊት ለማስቀጠል በጋራ መወያየትና መመካር አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ታሳቢ ያደረጉ ሁነቶች እየተካሄዱ እንደሚገኙ ነው ያብራሩት።

ብልጽግና ፓርቲ የትውልድ ፓርቲ ነው፣ዛሬ ላይ ቆሞ ለነገ አልሞ የሚሰራ ፓርቲ በመሆኑ በአጭር ስኬት የማይቆምና ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚተጋ ነው ብለዋል።

የፓርቲውን ምስረታ አስመልክቶ በሚከናወኑት ፕሮግራሞች የተመዘገቡ ስኬቶችን ከመዘከር ባለፈ እያጋጠሙ የሚገኙት ተግዳሮቶች ዙሪያ ከአባላት፤አመራር እና ከደጋፊዎች ጋር መወያየትና በፓርቲያችን ልዕልና መር ህልም ዙሪያ መግባባት መፍጠሩ አስፈላጊ በመሆኑ ፕሮግራሞች መዘጋጀቱንም አንስተዋል።

በክልላችን የፓርቲውን ምስረታ አስመልክቶ በታችኛው መዋቅሮች የተሰሩ ስራዎች ከጉብኝት እንዲሁም ፓናል ውይይት ከማድረግ ባለፈ ፓርቲው ሰው ተኮር እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ የበጎ አገልግሎት ስራዎች በመሰራት ጭምር በዓሉ እየተከበረ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም ሀገሪቱ እየገጠማት ካላት ችግሮች ተላቃ ለረጅም ዓመታት ያለመችውን የብልጽግና ጉዞ እንዲታረጋግጥ በችግሮች ላይ በመወያት የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ፈተናዎችን መሻገር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮግራሞች እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በዞኖች፤ወረዳዎች እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ፕሮግራሞች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ ያሉት አቶ ነጋ አበራ ክልላዊ ማጠቃለያ ህዳር ቀን 16/2017 ዓ.ም እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

ክልላዊ ማጠቃለያ ፕሮግራም የተለያዩ የፓርቲ አባላት፤የህብረተሰብ ተወካዮች፤ደጋፍዎችና አመራሮች በተገኙበት በዓሉ በተለያዩ ሁኔቶች እንደሚከበሩም አስረድተዋል።

በማጠቃለያው ፕሮግራም ከህዝቡ የሚነሱ የሰላም፤የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ዙሪያ በጋራ የሚንመካከርበት፤የውስጥ ችግሮችን እንዴት ማለፍ እንዳለብን የጋራ መግባባት የሚፈጠርበት፤የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠል ለቀጣይ ተሞክሮ ቀርበው ልምድ የሚንወስድበት መድረክ እንደሆነም ተናግረዋል።

በመጨረሻም አቶ ነጋ አበራ ፓርቲው ዓለምአቀፍ ስጋቶችን እየተጋፈጠ ዘመኑ የወለዳቸውን ፍላጎቶችን እያሳካ ወደፊት የሚሄድ፤የፓርቲ ህልውና ማስጠበቅ ሳይሆን የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰራ ፓርቲ በመሆኑ ፓርቲው የያዛቸው የረጅም ጊዜ ህልሞችና እቅዶች እንዲሳኩ የፓርቲው አባላት፤ደጋፊዎች እና አመራሮች የሚጠበቅባቸውን ሚና በተገቢው እንዲወጡ አሳስበዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *