የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በሸካ ዞን ተከበረ

Spread the love

የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅት በደማቅ ሁኔታ በቴፒ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ በብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ አለሙ እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስፋትና ክፍተቶችን በማረም ለሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምስረታ በዓል እንኳን አደረሳችሁ፤አደረሰን ያሉት አቶ አለማየሁ ፓርቲው በለውጥ ፈላጊ ዜጎች በሪፎርም የተመሠረተ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ጠቁመዋል።

ለፓርቲው ስኬታማ የ5 ዓመታት ጉዞ የአባሉና አመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አለማየሁ እንኳን ደስ አላችሁ፤ደስ አለን ሲሉም ገልጸዋል።

ለልዕልና መር ህልም ስኬት ብልፅግና ፓርቲ ቀን ከሌት እየተጋ ይገኛል ብለው ሰው ተኮር ተግባርም ከፓርቲው የትኩረት መስኮች ውስጥ አንዱ እንደሆነም አንስተዋል አቶ አለማየሁ።

“የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና”በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሠነድ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘርሁን አንደሞ እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን ውይይት ይደረጋል ተብሎም ይጠበቃል።

በፕሮግራሙ ላይ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ፣የዞኑ ዋና አፈጉባኤ አቶ ዮሐንስ ካሳሁንን ጨምሮ የዞን፣የሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር አመራሮችና የፓርቲው አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *