



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የ2017 ዓ.ም የበጋ መስኖ ልማትን በተመለከተ ለዞንና ለወረዳ ግብርና ባለሙያዎች በቦንጋ መዕከል የክህሎት ስልጠና ይገኛል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የእርሻ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ በስልጠናው ማስጀመሪያ ላይ እንደገለጹት፣ ክልሉ በሶስት ምርት ወቅቶች ላይ ሰብል የሚያመርት መሆኑን ገልጸው ከዚህም አንፃር በአንደኛ እና ሁለተኛ ዙር መስኖ ስራዎች የተጀመሩ መሆናቸውንና የእርሻ ስራው በሁሉም አርሶ አደሮች ተጀምሮ በመከናወን ላይ እንደለም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ ከወረዳ ና ከዞን 162 የግብርና ባለሙያዎች በሶስት ማዕከላት ማለትም በቦንጋ ፣ በታርጫና በሚዛን ማዕከላት ለዞንና ለወረዳ ግብርና ባለሙያዎች በቦንጋ መዕከል የክህሎት ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በቦንጋ ማዕከል የሚሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና የተጀመረ መሆኑን አቶ አሸናፊ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በመስኖ ልማት በበጋ መስኖ ስንዴ 12 ሺህ 100 ሄክታር በላይ መሬት በመሸፈን ከ100 ሺህ ኩንታል ምርት እንዲሁም በአትክልት 83 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመሸፈን 18.6 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን አብራርተዋል፡፡
ዛሬ በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ያለው የክህሎት ስልጠናም ይህንን ሊያሳኩ የሚገኙ ባለሙያዎች ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንና ቴክኖሎጂና ወቅቱን የደረሰበት ደረጃ መረጃ በማግኘት በተገቢው በመከታተል አርሶአደሮች በመደገፍ ኃላፊነታቸውን በየደረጃው እንዲወጡም አቶ አሸናፊ ክንፉ አሳስበዋል ፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ታገል ታምሩ በበኩሉ በቦንጋ ከተማ በሚሰጠው ስልጠና ከካፋ ዞንና ወረደዎች የተወጣጡ የግብርና ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆኑንና በስልጠናው የክህሎት ስልጠና ነው ያሉት፡፡
ስልጠናው በመስኖ ውሃ አጠቃቀም ስንዴና አትክልት አግሮኖሚ እና በዘርፉ የሚታዩ ችግሮች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰጠ ያለ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው የወረዳ ኤስ ኤም ኤስ ባለሙያዎች፣ የሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ፣የኤክስቴንሽን ኮሚንኬሽን ዘርፍ ና የሰብል ዘርፍ ባለሙያዎች ናቸው፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
