
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሳይፈቀድ የተያዙ እና በማስፋፋት የተያዙ ይዞታዎችን ለማስተካከል በመስተዳደር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 012/2015 እና መመሪያ ቁጥር 001/2015 በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ በተደነገገው መሠረት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ገልጸዋል።
የቢሮ ምክትል ኃላፊና የከተሞች መሬት ልማት ማኔጅመንት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ እንደገለጹት በክልሉ ሳይፈቀድ የታያዙ የከተማ መሬት ይዞታዎችን ለማስተካከል ትኩረት ተሰጥቷል።
በተደነገገው ደንብ እና መመሪያ መሠረት በክልሉ በሚገኙ በ18ቱ ከተማ አስተዳደሮችና በወረዳ ማዘጋጃ ቤቶች 32 ሺህ 682 ሳይፈቀድ የተያዙ የከተማ መሬት ይዞታዎችን ምዝገባ ማከናወን እንደተቻለ ጠቁመዋል።
የከተማ መሬት ሀብት ለከተሞች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝና መሠረታዊ ነው።ውድና ውስን የሆነው የከተማ መሬት ሀብትን በአግባቡ በማስተዳደር ሳይፈቀድ የተያዙ ይዞታዎችን መልክ በማስያዝ ከህገወጥነት መከላከልና ከተለያዩ ብልሹ አሰራሮች መታደግ ያሻል ብለዋል ኃላፊው ።
ደንብ እና መመሪያው ከተሞች በፕላን እንዲመሩ፤ለነዋሪዎች ብሎም ለእንቨስትመንት ምቹ እንድሆን፤ከተሞች የመሬት ሀብታቸውን በመለየት መረጃ አደራጅተው በተገቢው እንዲያስተዳድሩ፤ከተሞች ከመሬት የሚያገኛቸው ገቢ እንዲጨምር እና መሬትን በዘመናዊ ካዳስተር ለመምራት ከማገዝ ባለፈም አገልግሎቶችን ለማቀላጠፍ ያለው አበርክቶ ላቅ ያለ ነው።
የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ለከተማ መሰረት-ልማትና ህገወጥ የመሬት ወረራ ከመቀነስ ባሻገር የባለ ይዞታዎች መብትና ግዴታዎች እንዲጠበቅ እንደሚያግዝም አቶ ጫናቸው አስረድተዋል።
በክልሉ ሳይፈቀድ የታያዙ የከተማ መሬት ይዞታዎችን መልክ ለማስያዝ በተሰጠው ትኩረት በ18 ከተማ አስተዳደሮችና በወረዳ ማዘጋጃ ቤቶች 32 ሺህ 682 ሳይፈቀድ የተያዙ የከተማ መሬት ይዞታዎችን ምዝገባ ማከናወን እንደተቻለ ጠቁመዋል።
በዚህ መሠረት በካፋ ዞን 16ሺህ 231 በአምስት ከተማ አስተዳደር እና ማዘጋጃ ቤቶች፤ቤንች ሸኮ 9ሺህ 459 ከአራት ከተማ አስተዳደርና ማዘጋጃ ቤቶች፤ኮንታ 2ሺህ 350 ከሁለት ከተማ አስተዳደር እና ማዘጋጃ ቤቶች ፤ዳውሮ 1485 ከሁለት ከተማ አስተዳደር እና ማዘጋጃ ቤቶች፤ምዕራብ ኦሞ 735 ከሶስት ከተማ አስተዳደር እና ማዘጋጃ ቤቶች እንዲሁም ሸካ ዞን 2ሺህ 522 ከሁለት ከተማ አስተዳደር እና ለሎች ማዘጋጃዎች ምዝገባ ተከናውኗል ነው ያሉት።
ምዝገባውን ግለሰቦች በራሳቸው ሀላፊነት ወስደው እንደሚመዘገቡም የጠቀሱት አቶ ጫናቸው ወንድሙ የከተማውን ፕላን ወደ መሬት በማውርድ የሚከናወን ተግባር በመሆኑ የፕላን ስምምነት የሌላቸው እና በግዴታ መነሳት ያለባቸው ይዞታዎች ከሆነ ግለሰቦች የገነባውን ግንባታ በራሱ ገዜ ማፈርስ ስላለበት እና ሌሎች የህግ እርምጃዎችን ተግባራዊ እንድደርገበት ገንብዮች በተደነገገው ደንብና መምሪያ የተዘጋጀውን ማንዋል ተከትለው በራሳቸው ፊረማ አርጋግጠው ይመዘገባሉ ነው ያሉት።
በህግ ሳይፈቀድ የተያዙ እና በማስፋፋት የተያዙ የይዞታ መሬቶችን ህጋዊ ለማድረግ በሶስት ዓመት ውስጥ ለማጠናቀቅ ደንብና መመሪያ ወጥቶ ወደ ትግባር እንደተገባም አስረድተዋል።
መመሪያ እና ደንቡ በሁለት ምዕራፎች በተፈቀደው ጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ይህም በአንደኛው ምዕራፍ ህጋዊ ማድረግ እና በሁለተኛው ምዕራፍ ይዞታዎችን በቴክኖሎጅ ምዝገባ በማካሄድ የከተማ መሬቶችን ለመምራት አላማ ያደርገ መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል።
ሳይፈቀድ በመንግስት እውቅና ውጭ የተያዙ እንዲሁም ካሁን ቀደም ሳይፈቀድ በማስፋፋት ለተያዙ የወጣ መሆኑን ጠቅሰው በክልሉ በካዳስተር መሬታቸው ለማስተዳደር ለጀመሩት ከተሞች በተለይ በማስፋፋት የተያዙትን ህጋዊ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።
ደንብ እና መመሪያው ተግባራዊ እንዲሆን በሁሉም ዞኖች ግንዛቤ የሚፈጥር ለአመራሮች እና ለባለሙያዎች የተግባር ስልጠናዎች መሰጠታቸውንም ጠቅሰዋል።
በዚህም ሳይፈቀድ የተያዙ ይዞታዎች ምዝገባ፤ ሳይት በመውጣት ዘመናዊ የመሬት መሳሪያዎችን በመጠቀም የልዬታ ስራዎች መሰራቱን፤ሰነድ ማዘጋጀት፤የይዞታ ማረጋገጫዎች ለግለሰቦች መስጠት መቻሉንና በዚህም ስራው ያለበት ደረጃ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ አፈፃፀሞችን በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን ማረም በሚያስችል መልኩ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በ6ቱ ዞኖች የሚገኙ በ18ቱ ከተማ አስተዳደሮች እና የወረዳ ማዘጋጃ ቤቶችን ባካተተ መልኩ ዞናዊ ምዝገባዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል ኃላፊው።
ከከተሞች ፕላን እንስትቱውት ጋር በመቀናጀት 27ሺህ 347 ይዞታዎች ማጣራት፤ ለ20ሺህ 918 ይዞታዎች የሰነድ ማዘጋጀትና ከተዘጋጁት ውስጥ 12 ሺህ 875 ባለይዞታዎች ማዘጋጃ ቀርበው ይዞታቸውን እንዲቀበሉ መደረጉንም ኃላፊው ጠቁመዋል።
በዚህም 126ሺህ 498,376 ብር መሰብሰብ ተችላል ያሉት ሲሆን በቀጣይ በ1 ወር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ተግባሩ በንቅናቄ በሁሉም በክልላችን ማዘጋጃ ቤቶች እያተከናወነ ይገናልም ብለዋል።
ሳይፈቀድ የተያዙ መሬቶች መንግስት ህጋዊ ሲያደርግ ከዋጋ ተመን ጋር ባለው ጉዳዮች እና የሚወሰደው ረምጃ በሚመለከት ኃላፊው በሃሳባቸው ከቦታቸው በፕላን ምክንያት ለምነሱት ተለዋጭ ቦታ ማዘጋጀትና ንብረታቸው ካሳ መክፈል እንዲሁም እንደ ከተሞች ነባራዊ ሁኔታቸው የዋጋ ተመናቸውን በአካባቢ ሊዝ ዋጋ በመተመን ማስተናገድና ካሁን በፊት ሊዝ ተግባራዊ ላላደረጉት ከተሞች ደግሞ በከተማ ማዘጋጀትና ንብረታቸው ልዝ መነሻ ዋጋ ተመን እንዲያስተላልፊ ደንቡና መምረያው በተደነገገው መሠረት ተግባራዊ ይደርጋል ብለዋል።
ባለይዞታዎች ሙሉ በመሉ ቀርቦ ይዞታዎችን ያለማስመዘገብ፤የዘርፉ ባለሙያዎች እና የበጀት እጥረት እንዲሁም የአመራሩና የባለሙያዎች ቁርጠኝነት ማነስ እና ሌሎች ችግሮች ደንብና መመሪያው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ እንዳይሆን ተግዳሮት እንደሆነባቸውም ለአብነት ጠቅሰዋል።
ከመንግስት እውቅና ውጭ ይዞታዎችን መያዝና ማስፋፋት በከተማ ዕድገት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል ያሉት ኃላፊው ለአብነትም ከተሞች በተዘጋጀላቸው ፕላን መሠረት እንዳይመሩ እና የፕላን ጥሰት ማስከተል፤ከተሞች ከመሬት የሚያገኙትን ገቢ ማነስና ለመሠረተ ልማት ማነቆ መሆን ፤የከተሞች እድገት መቀጨጭ እንዲሁም ለህገወጥነት እና ለብልሹ አሰራሮች ክፊት ያደርጋልም ብለዋል።
ከተሞች በበቂ ሁኔታ ለነዋሪዎች የቤት ፍላጎትን ታሳቢ ባደረገ ይዞታዎችን ያለማዘጋጀት፤ከገጠር ወደ ከተማ የህዝብ ፍሰት መጨመር፤የከተማ መሬት በበቂ ሁኔታ ሰይዘጋጅ የተዘጋጁ ይዞታዎች ተወዳዳሪዎች የዋጋ መጨመር እና ሌሎች ጉዳዮች
በከተማ መሬት ላይ ህገ ወጥ እንድበራከት ከሚያደርጉ ነገሮች መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውም ኃላፊው አንስተዋል።
እነዚህንና የመሳሰሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በተደነገገው ደንብና መመሪያ መሠረት ከከተሞች ፕላን እንስትቱዩት ጋር በመሆን እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በክልሉ ሳይፈቀድ ይዞታዎችን የያዙ ግለሰቦች በማዘጋጃ ቤቶች በቀጣይ አንድ ወራት ውስጥ ተገኝተው ይዞታቸውን በተዘጋጀው ደንብና መመሪያ መሰረት ከባለይዞታዎች የሚጠበቀውን ግዴታ በመወጣት የይዞታ ማርጋገጫ እንዲወስዱም ኃላፊው አሳስበዋል።
