






“የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በዓሉ ከታችኛው የፓርቲ መዋቅር ጀምሮ እስከ ክልል ተቋማት ድረስ በተለያዩ ኩነቶቸ እየተከበረ የመጣ ነው፡፡ በደም ልገሳ ፣ በከተማ ጽዳት ፣ የባለፉት የፓርቲው ስኬቶችን አውደርይ በማዘጋጀትና ለሕዝብ በማስተዋወቅ እንዲሁም የበጎ አድራጎት ተግባራትን ማከናወን ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የፎቶ አውደ-ርዕይው የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ነው።
የፎቶ ኤግዚቢሽኑ በክልሉ በብልጽግና ፓርቲ መሪነት የተመዘገቡ የአስፈጻሚ ተቋማት፣ በክቡር ጠቅላይ ሚንስቴር ሀሳብ አመንጪነት የተከናወኑ የፌደራል ፕሮጀክቶች፣ ሰው ተኮር ስራዎች እና የካፒታል ፕሮጀክት የልማት ስራዎች አፈጻጸሞችን ያካተተ ነው።
በአውደ-ርዕይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ማስረሻ በላቸው፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ በላይ ተሰማ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና አባላት ተገኝተው ከፍተዋል።
በጌታሁን ግርማ
