


የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና “! በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ የማጠቃለያ ፕሮግራም በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት ምሥረታ በዓል ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርቲ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጀመረችው የለውጥ ጉዞ ውስጥ መሠረታዊ የሆኑ የኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችል መጠነ ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
ብዝሃነታችንን በአግባቡ በማስተናገድ ህብረብሔራዊ አንድነታችን በማጠናከር ገዢ ብሔራዊ ትርክት ለመገንባት ፈር ቀዳጅና ሀገር በቀል አስተሳሰብ የሆነውን የመደመር ዕሳቤ ዕውን በማድረግ ፍትሐዊና አካታች የፖለቲካ ተሳትፍና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እውን በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
ባለፉት 5 ዓመታት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ቢገጥሙንም እነዚህን ጫናዎች በየደረጃው አመራሩን፣አባሉንና ህዝቡን በማሳተፍ በጽናት በመሻገር ተጨባጭ የብልጽግና መሠረት እየጣለ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብለዋል።
የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የብዝሃ ክፍለ ኢኮኖሚ ልማት ፈለግ በመከተል በግብርና ኢንዱስትሪ ፣8በማዕድንና በቱሪዝምና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውንም አብራርተዋል።
የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባቶችን የሚያርቅ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ በማድረግ ባለፉት ከስድስት ዓመታት በፊት የነበረውን አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት በእጥፍ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እንደ ህዳሴ ግድብ ፣የቱሪዝም መደራሻዎች እንዲሁም የግብርናና የአካባቢ ጥበቃ ልማት ስራ አካል የሆነው የበጋ ስንዴ፣የአረንጓዴ አሻራ፣የሌማት ትሩፋት ፣የኮሪደር ልማት ስራዎችን ወደ ልማት በማስገባት ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።
በዲፕሎማሲው ረገድ የሀገርን ክብርና ጥቅም የሚያስከብሩ ከውጭ ጫና ራሳችንን ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል።
በክልሉ የኢኮኖሚ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ ፣ፍትሐዊ ልማትና ተጠቃሚነትን ለየሚያረጋግጥ የክልሉን ህዝብ የመደራጀት የፖለቲካ ጥያቄ በብልጽግና ፓርቲ ዕውን ሆኗል።
ባለፉት 5 ዓመታት በክልሉ ዘላቂ ሠላምና ልማት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገቡንም ተናግረዋል።
ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን በመከተል በስትራቴጂክ የግብርና ገበያ ምርቶች ውጤት መመዝገብ መቻሉንም አብራርተዋል።
ከክልሉ ምስረታ በፊት ተጀምረው የነበሩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት እንዲበቁ ማድረግ ተችሏል ሲሉም ተናግረዋል።
በመጪውርዕሰ መስተዳድሩ በቀጣይም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ ክልላዊ የጸጥታ ስራዎችን በዘላቂነት የማስቀጠል፣የዜጎችን ስራ ዕድል ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ፣ ህዝባዊ ቅቡልነትን የሚያረጋግጥ ስራዎችን መስራት፣የትምህርት ጥራት ማስጠበቅና በሽታን መከላከል መሠረት ያደረጉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላል ብለዋል።
በታጠቅ አበበ
