ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

Spread the love

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሹዌ ቢንግ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት በሁኔታዎች የማይቀያየር ስትራቴጂካዊ አጋርነት ደረጃ ላይ መድረሱን በመግለጽ፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን ለምታደርገው ጥረት የቻይናን ድጋፍ ጠይቀዋል።

ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ትብብር ፎረም (FOCAC) የተቀመጡ ግቦችን ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂዋ ጋር አጣጥማ እንደምትሰራም ገልጸዋል።

የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዙ ቢንግ በበኩላቸው፤ በሁለቱ አገራት ተደጋጋሚ ጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ ከልዩ መልዕክተኛው ጋር በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የጋራ ፍላጎቶች ላይ ምክክር ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *