





በኮሪደር ልማት ምልከታ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የቦንጋ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ እንቅስቃሴ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተማው ለኑሮ ምቹ እና ሳቢ እንዲሆን አየተሰራ የሚገኘውን የከተማ ኮርደር ልማት ለማሳለጥ ህብረተሰቡ ወስን ከማስከበር ረገድ እያደረገ ያለው ርብርብ እጅግ የሚመሰገን ነው ብለዋል።
ከተማው ሰፊ በመሆኑ ስራውን በውጤታማነት ለመምራት እንዲቻል በየደረጃው ከፋፍሎ የቅድሚያ የሚሰጠቸውን አካባቢዎች በፍጥነት እያጠናቀቁ መሄድ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ህብረተሰብ መወያየት ስለልማቱ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር እና የከተማውን ለኮሪደር ልማት የሚሆን ወሰን በማስከበር ህብረተሰቡ፣ የከተማው ነጋዴ እና መንግስት ሠራተኞች በስራው ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ሁሉም የሚመለከታቸው አመራሮች ስራው በተያዘለት ጊዜና ፍጥነት በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በምልከታው ላይ የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደን እና ሌሎች የክልል፣ የዞንና የቦንጋ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በተከተል ወልደሚካኤል
