






በኮንፈረንሱ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በበኩላቸው ሀገራችን ኢትዮጵያ በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ አንድነት ያላት ቢሆንም ባለፉት ዓመታት ውስብስብ ፈተናዎች ሲጋጥሟት እንደቆየ ገልፀው ፈተናዎችን በፅናት በማለፍ ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።
በዞናችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ማስቀጠልና ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ ከአመራሩና አባሉ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን ገልፀው ከምንም በላይ በአካባቢያችን ያሉትን ፀጋዎች በመጠቀምና ማህበረሰቡን በማስተባበር ማልማት ይገባናል ብለዋል።
እንደ ሀገር የተጀመረውን ሁለተናዊ ብልፅግናን በዞኑ የማረጋገጥ ተግባር በቁጭት በመምራት በየዘርፉ የተጀመሩ የለውጥ ውጥኖችን በተነሳሽነትና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አክለው ገልፀዋል።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ አለሙ በዞኑ ውስጥ ፓርቲውን በጠንካራ አመራርና አባላት ለመገንባት ጥልቅ ግምገማ በማድረግ ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ ለማሻሻል የቅድመ ጉባኤ ዝግጅት ውይይቶችና ግምገማዎች በየደረጃው ሲካሄዱ መቆየታቸውን አብራርተዋል።
አመራሩና አባሉ የጠራ አመለካከት በመያዝ ከስነ-ምግባር ችግሮች በመላቀቅ በጠንካራ ውስጠ ፓርቲ ትግል ጠንካራ ተቋም በመፍጠር የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የተግባር ውጤታማነቱን ሊያረጋግጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።
“ከቃል ወደ ባህል” የሚለው ዕሳቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የፓርቲያችን ብልፅግና ቃልን በተጨባጭ በተግባር የማሻገር ባህል ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር አስተዋጽኦ የጎላ በመሆኑ ቃልን ወደ ተግባር መቀየር ባህል ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አብራርተዋል።
ለኮንፈረንሱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ያቀረቡት በብልጽግና ፓርቲ ሸካ ዞን ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘርሁን አንደሞ ብልጽግና ፓርቲ በሪፎርም የመጣ ፓርቲ መሆኑን ገልፀው በተለይም የሀገሪቱንና የህዝባችንን ህልም ከዳር ለማድረስ ጠንካራ ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን መሠረት በማድረግ ሀገራዊ ትርክት መገንባት የቻለ ፓርቲ ነው ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት ብልጽግና የሀገሪቱን የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶችን በመጠገን ወደ ተሟላ ብልፅግና ጉዞ አሸጋግሯል ያሉት አቶ ዘርሁን ስኬቶችን ባህል አድርጎ በማስቀጠልና የህዝቡን ሁለንተናዊ ፍላጎት ባማከለ መልኩ በመስራት የብልጽግና እሳቤዎችን ከግብ ለማድረስ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት በብልፅግና ዘመን የሚታይና የሚጨበጥ ለውጥ መመዝገቡን ጠቁመው አሁን የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን በአካባቢያችን ባህል ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል።
ብልፅግና ከቃል በላይ በርካታ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አከናውኗል ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ በዞኑ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቆ ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጥና ፓርቲያችን ብልፅግና ለህዝባችን ሰላምና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ያቀዳቸው ሰፊ ዕቅዶችን ወደ ተግባር እንዲቀይር ጠይቀዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ ቀጣይ ሸካ ዞንን ወክለው በሀገርና ክልል አቀፍ የብልፅግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮችን በመምረጥ ኮንፈረንሱ ተጠናቋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
