ፓርቲያችን ብልጽግና ባሳለፍናቸው አመታት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱ ተገለፀ

Spread the love

በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት “ከቃል እስከ ባህል “በሚል መሪ ቃል 2ኛውን የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ቅድመ ጉባኤ የማጠቃለያ ኮንፈረንስ በጀሙ ከተማ አካሂደዋል።

ጉባኤው በተለያዩ የባህላዊ ዉዝዋዜ የታጀበ መሆኑ ተጠቅሷል።

በኮንፍረንሱ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ ፓርቲያችን ብልጽግና በባለፉት አመታት በርካታ ውጤታማ ሰው ተኮር ስራዎች መስራቱ እና አሁንም እየሰራ መሆኑ አስገንዝበዋል።

አክለው ፓርቲ በሀገራችንን ኢትዮጵያን ለመለወጥ፣በአለም አቀፍ ደረጃ የምትከበር ሀገር ለማድረግ ልማቷ የተፋጠነ እንዲሆን የሚያደርግ አደረጃጀት በመፍጠር ያሉትን ነጠላ ትርክቶች በመተው የሚያስማማ የጋራ ገዢ ትርክትን በመገንባት ተስፋ ሰጪ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየ ሀገር በቀል ፓርቲ መሆኑ አዉስቷል።

ፓርቲያችን ብልጽግና ባሳለፍናቸው አመታት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራትን ሲፈጽም እንደቆየ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ምስክሮች ናቸው ያሉት ዋና አስተዳዳሪ ቃሉን በተግባር እየፈጸመ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ብልጽግና የጀመራቸውን የልማት ጉዞዎች ለማስቀጠል ይህ ጉባኤ ጠቃሚ ነው ያሉት አቶ ጌታቸዉ በቀጣይም ይህንን የወንድማማችነት የአብሮነት ጉዞ ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ በድሉ መዓዛ እንደተናገሩት ፓርቲው የሰው ተኮር ስራዎችን ለማገዝ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው ብሎ ተነስቶ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል ብልዋል።

ፕሮጀክት ጀምሮ መጨረስን ባህል ያደረገ፣ የአረንጓዴ አሻራ ቅቡልነት ፤አረጋውያን የመደገፍ ፤የማዕድ ማጋራት ሥራዎች ፣ የሌማት ትሩፋት እና ሌሎች ተግባራት ተግባራዊ ማድረጉ ለዚህ በምሳሌነት የሚጠቀሱ መሆናቸው አክሎበታል።

በመድረኩ የዞኑ የኢንስፔክሽን እና ሥነምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ም/ሃላፊ አቶ አቶ ዉብሸት መኮንን በበኩላቸው በባለፉት ወቅት የተሰሩ ሥራዎች የተመዘገቡ ስኬቶች ለጉባኤው ተሳታፊዎች አቅርቧል።

በዞኑ ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቅ እና የህዝብ ተጠቃሚነት ላይ የተሰሩ ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው ተሳታፊዎች አንስተዋል።

በመጨረሻም በጉባኤው በቀጣይ በክልል ደረጃ በሚካሄደው ኮንፍረንስ ላይ የሚሳተፉ 69 አባላት እና በፌዴራል ደረጃ በሚደረገው ላይ የሚሳተፉ 5 አባላት በመምረጥ ተጠናቋል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *