የተደራጁ ወጣቶችና ሴቶች በበጋ መስኖ ተግባር በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳተፉ ይገኛሉ፦አቶ ማስረሻ በላቸው

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው፤ በዳውሮ ዞን የተደራጁ ወጣቶችና ሴቶች በበጋ መስኖ ተግባር በከፍተኛ ሁኔታ እየተሳተፉ እንደሚገኙ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በዳውሮ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አትክልት፣ስራስርና ፍራፍሬ በማልማት ተጠቃሚነታቸው እየተረጋገጠ የመጡ የተደራጁ ወጣቶች አትክልትና ፍራፍሬ ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የአከባቢውን ፀጋ ወደ ሃብት በመለወጥ የሚያኮራ ተግባር በመፈፀም ላይ ይገኛሉ ብለዋል አቶ ማስረሻ በላቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *