በዋሽ ፕሮግራም በክልላችን መጠነ ሰፊ ስራዎችን መስራት ተችሏል፡፡ ኢንጂነር በየነ በላቸው

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያውያ ህዝቦች ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በአሃዳዊ ዋሽ ምዕራፍ 2 ፕሮግራም አፈፃፀም ላይ ከባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጥ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር በየነ በላቸው፣ በአሃዳዊ ዋሽ ምዕራፍ 2 ፕሮግራም በክልላችን በውሃ፣ በጤናና በትምህርት መስኮች በጣም መጠነ ሰፊ ስራዎችን መስረት ተችሏል ብለዋል፡፡

ፕሮግራሙ ለመንግሥት ትልቅ አጋዥ የሆነ ፕሮግራም መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር በየነ በውሃ፣ በጤናና በትምህርት መስኮች በዚህ ፕሮግራም ስራዎች እየተሰሩ ማምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ፕሮግራም እየወረደ ያለው ሀብት ለማህበረሰቡ ጥቅም ላይ እንዲውል እየተመራ ያለበትን ሂደት በየጊዜው በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን በጋራ እያስቀመጡ መሄድ አስፈላጊ መሆኑን ኃላፊው ገልጿል፡፡

ዋሽ ፕሮግራም በ5ቱ መርሃ ግብር የተከናወኑ ተግባራት እንዳሉና ፕሮግራሙ በተያዘው 2017 አመት የሚጠናቀቅ በመሆኑ የታቀዱ ተግባራትን በትኩረት መፈጸም እንዳለበትም ኢንጂነር በየነ አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ ከክልል የፕሮግራሙ ስትሪንግ ኮሚቴዎች፣ የሁሉም ዞንና ወረደዎች የፕሮግራሙ ባለድርሻ አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

መድረኩ በአሁኑ ሰዓት በአሃዳዊ ዋሽ ምዕራፍ 2 ፕሮግራም የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም እየቀረበ ሲሆን በቀረቡት አፈፃፀም ሪፖርቶች ላይ ውይይት ተደርጎ መድረኩ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *