

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብትና የአንድነታቸው ትልቁ ማሳያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ያለ አንድ ብር የውጭ እርዳታና ብድር፣ በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ቁርጠኛ አቋም እና በጋራ የመቆም ጥበብ ብቻ እውን የሆነ ድንቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አፅንኦት ሰጥተው እንደተናገሩት፣ ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት ያለ ብድርና እርዳታ በራሱ አቅም ያሳካ መንግሥትና ሕዝብ ሌሎች ፕሮጀክቶችን አይሰራም ሊባል አይችልም።
የሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ኢትዮጵያ ጨክና ከተነሳች እና በአንድነት ከቆመች የማይቻል ነገር እንደሌለ ለዓለም ያስመሰከረችበት ታላቅ የድል አርማ ሆኖ ለትውልድ ይተላለፋል ብለዋል።
