በ9 ወራት አፈጻጸም የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የዋሽ እና ገበያ መር ሳኒቴሽን የ2017 ዓ/ም የ9ወር የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የክልሉ ጤና ቢሮ የንጽህና አጠባበቅ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ መሠረት በ2030 ላይ ሁለንተናዊ ዘላቂነት ያለው ፣ ለአየር ንብረት የማይበገር፣ ፍትሐዊ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ተመጣጣኝ ዉሃ ለሁሉም ተደራሽ በማድረግና የተሻሻለ፣ ዝቅተኛ የአካባቢ ተጽዕኖ ያለው የአካባቢ ጽዳትና የንጽህና አጠባበቅ ዓላማ በማድረግ እየሰራ መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል ።

ስኬታማነቱን ለማረጋገጥ ከብዙ ባለድርሻ መ/ቤቶች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን በማስታወስ በ9ወራት አፈጻጸም የተመዘገቡ ውጤቶችና የታዩ ጉድለቶቹ ላይ ውይይት በማድረግ በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የባለድርሻ አካላት ድርሻቸውን መውሰድ እንደሚገባ አቶ ኢብራሂም በአጽንኦት ተናግረዋል።

በክልሉ 13 የገጠር ወረዳዎችና 1 የከተማ አስተዳደር በOne Wash ፕሮግራም፣ 4 ወረዳዎች በዩኒሴፍ፣2 ወረዳ በኮ-ዋሽ፣ 7 ወረዳዎች የሳኒቴሽን ማርኬቲንግ ማህበር ተደራጅቶ የሳኒቴሽን ምርት በማምረት እየሰሩ መሆኑን በማንሳት አፈጻጸሙን በጋራ በመገምገም ከጥንካሬው ተሞክሮ ለመውሰድና ጉድለቶችን ማረም ያለመ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የመጸዳጃ ቤቶች ሽፋንን በማሳደግ በሜዳ ላይ ከመጸዳዳት ነፃ በማድረግ የተላላፊ በሽታዎች ጫና ለመቀነስ ከፍተኛ ድርሻ እንደለው የቢሮ ኃላፊው ጨምሮ አንስተዋል።

የዞኑ የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ሪፖርት ለተሳታፊዎች እየቀረበ ይገኛል ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *