ከኦም ባንክ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል፦አቶ ማስረሻ በላቸዉ

Spread the love

የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ቁጠባ፣ብድር ሥርጭት እና አመላለስ ላይ ዓላማ ያደረገ የምክክር መድረክ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ሥራና ክህሎት ፣ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ኦሞ ባንክ በጋራ አዘጋጅነት በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ነው።

በምክክሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ እንደገለጹት፤ከኦም ባንክ ጋር ተቀናጅተው በመስራት የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

አሞ ባንክ በክልሉ ከ350 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ልያደርግ የሚችል 5.7 ቢሊዮን ብር በማሰራጨት ለሥራ ዕድል ፈጠራ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን ሚናውን በከፍተኛ ሁኔታ እየተወጣ መሆኑንም ገልጸዋል ።

ከተሰራጨው ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር 4 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ተመላሽ መደረጉን ያብራሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ተሰራጭተዉ ያልተመለሰ አንድ ቢሊዮን ብር በአግባቡ ተሰብስበዉ አገልግሎት ላይ እንዲዉል ሁሉም እንዲረባረብ አሳስበዋል።

የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም አላሮ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አምስት ዲስትሪክት እና 49 ቅርንጫፎች በመክፈት ከ360 ሺህ በላይ ደንበኞችን በማፍራት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።

የባንኩን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ እና አገልግሎቱን በማዘመን የሥርጭት አድማሱን ለማስፋት በትኩረት እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

በመድረኩ የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አብይ አንደሞ በክልሉ ከተረጂነት በመላቀቅ ለዜጎች የሥራ ዕድልን በመፍጠር ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ እንዳለ ተናግረዋል።

ኦሞ ባንክ ባለፉት ጊዜያት ለዜጎች ለሥራ ዕድል ፈጠራ የገንዘብ ምንጭ አቅም በመሆን የድርሻውን በመወጣቱ አመስግነዉ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ተሰራጭተዉ ያልተመለሱ ብድሮችን ለማስመለስና የዜጎች የቁጣብ ባህል በማሻሻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት ይሰራል ብለዋል የቢሮ ኃላፊዉ።

በመድረኩ የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትልና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አየለ ለምክክር መድረኩ የተዘጋጀውን ሰነድ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በመድረኩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣የኦሞ ባንክ አመራሮች የዞንና አስተዳዳሪዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *