መንግሥት ከግሉ ዘርፍ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ፍትሀዊና አካታች ማህበራዊ ልማት ለማረጋገጥ እየተጋ ነዉ። ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

መንግሥት ከግሉ ዘርፍ ጋር ተቀራርቦ በመስራት ፍትሀዊና አካታች የማህበራዊ ልማት ለማረጋገጥ እየተጋ እንደሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት “የብልጽግና ጉዟችንና የንግዱ ማህበረሰብ ሚና” በሚል መርህ-ቃል ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር እየተካሄደ በሚገኘው ክልላዊ ማጠቃለያ ውይይት ላይ ነው።

የተረጋጋ የአንድ ማህብረሰብ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ግንባታ ለማረጋገጥ በሚደረገው ያልተቋረጠ ጥረት ውስጥ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና የጎላ መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ቀጣይነትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ግንባታ በመደገፍ፣ ምርትና አግልግሎት በማቅረብ ገበያን በማረጋጋት፣ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፈጠር እንዲሁም ማህበረሰባዊ ሀላፊነት በመወጣት የንግዱ ማህበረሰብ የጎላ ድርሻ እየተወጡ እንደኾነም ጠቁመዋል።

በመንግሥት በኩል የንግድ ማህበረሰብ በመደገፍ ዘርፉን ለማሳለጥ የሚያስችሉ መጠነ ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ መኾኑን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ከነዚህም ውስጥ በዋናነት የህግ ማዕቀፎች ማሻሻያ፣ ማበረታቻዎች፣ የታክሲ እፎይታ እንዲሁም በተለያዩ ነኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰሩ የግሉ አልሚዎች የሚደረገው ድጋፍ የሚጠቀስ እንደሆነ አብራርተዋል።

የመንግሥት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ያስገነዘቡት ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር መዋቅሮችም የዘርፉን ችግሮች ቀርበው በመፈተሽ መፍተሔ ማበጀትና ችግሮችን በምዛዊነት መፍታት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

ሀገራዊ ማህበረሰባዊ ኃላፊነትን በአግባቡ የሚወጡ የንግዱ ማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉ ሁሉ አልፎ አልፎ በዘርፉ የሚስተዋለው ህገወጥ ተግባራት፣ ህገወጥ ንግድና የገብ ሰወራ እንዲሁም ምርትን ባልተገባ መልኩ በማከማቸት በገበያ ውስጥ እጥረት እንዲፈጠር አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ተግባራት ፈጥኖ መታረም እንደሚገባ አሳስበዋል።

ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በራሱ በንግዱ ማህበረሰብ ውስጥ ጤናማ ያልሆነ የንግድ አከባቢ ከመፍጠር ባሻገር በሸማቹ ዘንድ ያልተገባ የገበያ ዋጋ ጭማሪ በማድረግ የኑሮ ውድነት እና የገበያ ያለመረጋጋት የሚፈጥር መኾኑን ተናግረዋል።

ስለሆነም የዘርፉ ተዋናዮች በሃገራዊ ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ዙሪያ በቅርበት በመመካከር የተረጋጋ የገበያ ስርዓትን በመፈጠር ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት መረጋገጥ ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አስገንዝበዋል።

የክልሉ የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ የመወያያ ሰነድ እያቀበ የሚገኝ ሲሆን ውይይቱ በመንግሥት በኩል የተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች እና በንግድ ማህበረሰብ በኩል በሚቀሩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት የጋራ መግባባት ለመፈጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *