ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ




ርዕሰ መስተዳድሩ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት
➣ በመኸር እና በበልግ በዋና ዋና የአዝርዕት ሰብሎች 688 ሺ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ፡፡
➣ 19 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰብ ተችሏል፡፡
➣ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭት አኳያ 190,013 ኩ/ል ተሰራጭቷል ፡፡
➣ በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት 1,073 ንዑስ ተፋሰስ ወይም 217,384 ሄ/ር ማልማት ተችሏል ፡
➣ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ በክረምት የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው 129,102,135 ተተክለዋል ፡፡
➣ የአንድ ጀንበር ተከላ 20,512,583 ችግኞች ተተክለዋል ፡፡
➣ 54 ሺ 795 ሜትሪክ ቶን የታጠበና ያልታጠበብ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብም ተችሏል
➣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ለማሻሻል በብሔራዊ የገጠር መሬት አስተዳደር መረጃ ስርዓት 122,469 ማሳዎች በ8 ወረዳዎች በ141 ቀበሌዎች ገብተዋል ፡፡
➣ 1,915,110 የአንድ ቀን ጫጩት እና 2.7 ሚሊየን ቀብና ኮክኔ ማሰራጨት ተችሏል ፡፡
➣ 92,632 የተለያዩ ቀፎዎችን በማሰራጨት 70,434 ቶን የማር ምርት ማምረት ተችሏል፡፡
➣ የሌማት ትሩፋት ስራዎች ውጤታማ ከማድረግ አኳያ 266 የወተት መንደሮች ፤447 የዶሮ መንደሮች 977 የንብ ሀብት መንደሮች 73 የዓሳ ግብርና ፣መንደሮች ተደራጅተዋል ፡፡
➣ 52,276.6 ቶን የቅመማ ቅመም ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ፡፡
➣ 6,654 ቶን የሻይ ምርት ለገበያ ማቅረብ ተችሏል፡፡
➣ ከአፈር ማዳበርያ ዕዳ አመላለስ ጋር በተያያዘ ከ2014/15 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2016/17 በጀት ዓመት ብር 1,112,969,054.96 ዕዳ ለማስመለስ ታቅዶ ብር 582,950,708.43 (52%) በማስመለስ ማቀናነስ እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡
➣ ከደን አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ስራዎች አኳያ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ለ176 አዳዲስ የልማት ፕሮጀክቶች የአካባቢና ማህበራዊ የተፅዕኖ ጥናት ሰነድ ገምግሞ ይሁንታ ፍቃድ ተሰጥቷል ፡፡
➣ በደን ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም፣ በበጀት ዓመቱ በበልግና በመኸር በድምሩ 80.5 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል ፡፡
➣ የችግኞችን የመጽደቅ አቅማቸውን ለማሻሻል 131 ነባር ችግኝ ጣቢያዎችን ማጠናከር ተችሏል
6 አዲስ ሞዴል የችግኝ ጣቢያዎችን ማቋቋም መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸዉ አመልክተዋል።
በታጠቅ አበበ
