የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

Spread the love

ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤውን በታርጫ ከተማ እያካሄደ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የአስፈጻሚ ተቋማትን የ2016 በጀት ዓመት የአፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ነው ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለምክርቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች በተደራጀ መልኩ በመምራትና ውስን የመንግሥት ሃብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ከማድረግ አንጻር በልዩ ትኩረት ተግባራት መከናወናቸውን አብራርተዋል ፡፡

በዚህም በየሥራ ዘርፉ ያሉ የልማት ኃይሎችን አቀናጅቶ የተደራጀ የልማት አቅም በመገንባት፣ በክልሉ በሠላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ተጨባጭ ለውጦችን ተመዝግበዋል ብለዋል፡፡

ክልሉ በይፋ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ዐበይት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ እንዲሁም በአስተዳደርና አመራር ዘርፍ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው አመላክተዋል ፡፡

ለአብነትም ካነሷቸው ነጥቦች 419,638 የክልል፣ የዞን፣ የከተማ አስተዳደር፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንዲያገኙ መደረጉን አብራርተዋል፡፡

ወቅታዊ ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ከክልል ማዕከል ጀምሮ በየደረጃው የሚገኝ 2,221 አመራሮችን የመገምገምና የማጥራት ስራ በልዩ ሁኔታ መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡

በአመራር ብልሽት ውስጥ የገቡ 196 አመራሮች ከኃላፊነት እንዲነሱ፣176 አመራሮች የቦታ ሽግሽግ እንዲያደርጉ 442 አመራሮች ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተደርጓል ሲሉም ገልጸዋል ፡፡

ዘላቂ ሠላም ከማረጋገጥ አንጻር የጸጥታ ስጋት ባለባቸው አካባቢዎች ተከታታይ የማህበረሰብ ውይይት በማድረግ ፣ የታችኛው አስተዳደር እርከን የጸጥታ መዋቅር መልሶ የማደራጀት ስዎች በትኩረት መከናወናቸውንም በሪፖርቱ አመላክተዋል ፡፡

የዕዳ ጫናን ከመቀነስ አኳያ 1.3 ቢሊየን ብር ዉዝፍ የግብዓት፣የማህበራዊ ዋስትናና የደመወዝ ጥሬ ገንዘብ ብድር መመለሱን ጠቅሰዋል።

ክልላዊ የኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እና የግንባታ ዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን በማቋቋም ኃላፊነቱን እንዲወጣ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሁሉም ብዝሃ ማዕከላትና ተደራሽ ከተሞች የህንጻ ዲዛይን ስራ ተጠናቆ የግንባታ ግዥ ለማከናወን የሚያስችል አማካሪ ቅጥር ሥራ ተከናዉኖ ወደ ስራ መግባቱን ሪፖርት አድርገዋል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *