







የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክርቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው ።
የምክርቤቱን የ2016 በጀት ዓመት የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት ለጉባኤው ያቀረቡት የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጸሐይ ዳርጫ ምክር ቤቱ በበጀት ዓመቱ መደበኛ ጉባኤዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል ።
በክልሉ አስፈላጊ የሆኑ አዋጆችን፣ ደንቦችን በማውጣትና በምክርቤት አባላት በማስጸደቅ ስራ ላይ እንዲውል መደረጉንም ምክትል አፈጉባኤዋ አብራርተዋል።
በበጀት ዓመቱ የአስፈጻሚ አካላት የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በመገምገምና ግብረመልስ በመስጠት የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ሚናውን ተወጥቷል ብለዋል።
የህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮችን በማመቻቸት ዜጎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዲያነሱ በማስቻል በየደረጃው ባሉ ተቋማት ፈጣንና ቀልጣፋ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኙ በትኩረት የተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
የምክር ቤቶች የጋራ ምክክር መድረክም በዕቅዱ መሰረተ መከናወኑንም ገልጸዋል።
ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመቀናጀትም የድጋፍና ክትትል ስራ ተሰርቷል ብለዋል።
በቀረበዉ ሪፖርትም የምክር ቤት አባላት የተለያዩ ጥየቄዎችንና አስተያየቶችን አቅርበዋል።
የክልሉ ምክርቤት ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስተው በዋና አፈጉባኤ በተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ምላሽ ተሰጥቦቸዋል።
በዚህም የህዝብ አስተያየት መድረኮችን ማስፋት፣ በታኛዉ ምክር ቤት የሚወጡ ህጎችን የተፈጻሚነት ወሰን ማየትና የኦዲት አስመላሽ ግብረ ኃይልን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።
በቀረበዉ የምክር ቤት ሪፖርት ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ የቀረበውን አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል።
በታጠቅ አበበ
