







ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ለከተሞች እንደሀገር ባዘጋጀው ምዘና መስፈርት መሠረት ተመዝነው ከ26 ከተሞች አንዱ በመሆን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ሽልማቱን አግኝቷል።
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ከተለያዩ ከተሞች ከተወጣጡ ከአቻ ከተማ ከንቲባዎች ጋር ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ግንባታ ጉብኝት የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ የተሳተፉ ሲሆን በኢትዮጵያ ከተመረጡ ከተሞች አንዷ የቦንጋ ከተማ እንደሆነች ገልፀው ከተማ አስተዳደሩ በተለያየ ጊዜያ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ላይ ሲሳተፍ መቆየቱን ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ ተሞክሮ በመውሰድ በቀጣይ አጠናክሮ ለመሰራት ጠቃሚ ልምድ ልውውጥ ማግኘታቸውን የተናገሩት አቶ አስማማው ከኮሪደር ልማት ጉብኝት በኃላ በነበረው ግምገማ መደረክ በከተማው የተጀመረው የኮርደር ልማት እንቅስቃሴ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት ለቀጣይ አቅጣጫ መቀመጥ መቻሉን አስረድተዋል።
ለገቢ ሪፎርም ስራዎችና የከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ለማዘመን እንዲውሉ የተበረከቱ የዲስክቶፕ ኮምፒውተር፣ፕሪንተር፣ የፕሪንተር ኬብል እና ስካነር አቶ አስማማው ተረክበዋል።
ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ1.4 ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣል ያሉት አቶ አስማማው ለተደረገላቸው ስጦታም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አመስግነዋል።
