


ኢትዮጵያን በተለያዩ ሀገራት እንዲወከሉ አዲስ ለተሾሙ አምባሳደሮች ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ፥ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የሀገር ፍቅርን በማስቀደም በህዝብ የታመነ አደራን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
አምባሳደሮቹ እውቀትን ከሀገር ፍቅር ደርበው፣ ለብሔራዊ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት የአገልጋይነት ክብርን ማሳየት እንደሚገባቸውም አምባሳደር ታዬ ገልፀዋል።
ስልጠናው ሀገሪቱ ከምታራምደው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በመነሳት እና የውስጥም የውጭም ተገዳዳሪ ነገሮችን በመከላከል የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ያግዛል ብለዋል።
አምባሳደሮቹ በሀገር ፍቅር እና በእውቀት የታነፁ፣ የመሪነት ክህሎትን የተላበሱ እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮችን የተረዱ፤ ሀገርን ከሀገራት ጋር በየተለየ አስተሳሳሪ መሆን እንደሚጠበቅባቸውም አምባሳደር ታዬ አሳስበዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።
