የህዝቦች ትስስር የተጠናከረበት የሸኮ ብሔር ድንቅ ባህላዊ ዕሴት – ቲካሻ ቤንጊ

Spread the love

የበለፀገች የጋራ ሀገር ለመገንባት እና የህዝቦች አንድነትን ለማጠናከር ከነጠላ ትርክት በመላቀቅ አርበኝነትን የሚያጎሉ አሰባሳቢ ትርክቶችን ለትውልድ ማሳወቅ፣ ማስተማር እና ማስረጽ ወቅቱ የሚፈልገው የሀሳብ ልዕልና ነው።

ህብረ ብሄራዊት በሆነችው ኢትዮጵያ ህብረብሄራዊ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን የሚያጎሉ ፣ አብሮነትን፣ እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሚያስችሉ እንዲሁም ብሔራዊነትን የሚያጎለብቱ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

የሸኮ የባህል አባቶች በብሔረሰቡ አዲስ ዓመት (ቲከሻ ቤንጊ) ያለፈውን ዓመት እንዴት እንዳሳለፉ ወደኃላ የሚመለከቱበትና መጪው ቤንጊ (አመት) የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነት፣የመተሳሰብ፣የልማትና አብሮ የማደግ እንዲሆን በጋራ በመኾን የሚመክሩበት ታላቅ በዓል ነው።

ቲካሻ ቤንጊ ለአዲሱ ዓመት አዲስ ተስፋ የሚሰንቅበት ፣የተጣላ የሚታረቅበት፣በጋራ መዓድ የሚቆረስበት፣ መተሳሰብ እና አብሮነት እሴት የሚጎለብትበት የሸኮ የማኅበረሰብ ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብት ነው።

በሸኮ ከተማ ዛሬ በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው በዚህ በዓል ከክልሉ የተለያዩ አከባቢዎች የህዝብ ተወካዮች፣ የባህል ቡድን በክነት ባንድ ደምቀው ኢትዮጵያዊነት በተግባር እያሳዩ፣ በዓሉ የመሰባሰብ እና የፍቅር መኾኑን በተግባር አሳይተዋል።

ኢትዮጵያ በአብሮነት ተዋደው እና ተጋምደው የሚኖሩ የጋራ ባህል እና ዕሴትን የሚጋሩ ህዝቦች ያሏት፣ የተለያዩ እምነት ተከታዮችን የምታስተናግድ፣ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ ታላቅ ሀገር ናት ፤ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም የብዝሀ ማንነት የሚታይበት ክልል ነው።

በትላንት ታሪካችን ፣ በዛሬ ወረት እና ስኬት ፣ እንዲሁም በነገ ራዕያችን በማስተሳሰር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን በጋራ ለመገንባት በሚደረገው የጋራ ጥረት በህዝቦች መካከል አንድነትና ፍቅር የሚሰብክ መሰል ህዝባዊ በዓላት ልዩ ትርጉም እንዳለው ይታመናል።

በሸኮ ከተማ በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው የቲካሻ ቤንጊ በዓል የታየው የህዝቦች ትስስር፣ አንድነት፣ መሰባሰብ እና ፍቅር በማጠናከር ለብሄራዊ ገዢ ትርክት ግንባታ የበኩላችንን እንወጣ።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *