



በመማር ማስተማር ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ የትምህርት ስራን ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቤሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ደስታ ገለጹ
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከዩኒሴፍ በመተባበር ተደጋግሞ መጠቀም የሚያስችል የንጽህና መጠበቂያ ቁስ ማምረትና መጠቀም ዙሪያ ለተማሪዎች የክህሎት ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠና መርሃ ግብር የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ዶ/ር ደስታ ገነሜ እንደገለጹት የትምህርት ስርቱን ውጤታማ ለማድረግ የክህሎትና የዕውቀት ክፍተቶችን በጋራ መቅረፍ ሲቻል መሆኑን ገልጸዋል።
ለተከታታይ ቀናት የሚሰጠው የክህሎት መር ስልጠና ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸው በአግባቡ እንዲከታተሉና ይከሰት የነበረውን መጠነ ማቋረጥን ለማስቀረት የሚያስችል እንደሆነ ገልጸዋል።
በትምህርት ስርዓቱ ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት ተማሪው፣ መምህራንና ወላጆች እያደረጉት ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
ሴቶች በትምህርታቸው ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ ለችግሮቻቸው መፍትሔ ሊሆን የሚችል ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
በክልሉ ትምህርት ቢሮ የዩኒሴፍ አስተባባሪ አቶ ካሳሁን ዱባለ በስልጠና ላይ እንደገለጹት ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ተማሪዎች የወር አበባ በሚያዩበት ጊዜ ከትምህርት ገበታቸው መቅረት እንዳይችሉ ይህ የሚሰጠው ስልጠና ችግር ፈች እንደሆነ ጠቅሰዋል።
ተደጋግሞ መጠቀም የሚያስችል ንጽህና መጠበቂያ ቁስ ማምረትና መጠቀም የክህሎት ስልጠና ከትምህርት ስብራትን ከሆኑት ውስጥ መጠነ ማቋረጥን ለመከላከል አስቻይ ሁኔታ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
ከዩኒሴፍ በሚደገፍ ከ14 ወረዳዎች ከ95 ትምህርት ቤት በላይ ከ200 በላይ ለተማሪዎችኝ የክህሎት ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በስልጠናው በክልሉ በሚገኙት ዞኖች የተውጣጡ የስርዓተ ጾታ ክበብ አስተባባሪ መምህራንና የክበብ ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲሉ አሳውቀዋል።
በቀጣይ ይህንን ተግባር ማሳለጥ ያስችል ዘንድ የክህሎት መር ስልጠናዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች በዩኒሴፍ በኩል ቀርበው ለትምህርት ቤቶች እንደሚሰራጩ አቶ ካሳሁን አስረድተዋል።
በክልሉ ተክኒክና ሙያ ኮሌጆች በጨርቃጨርቅ ስራ ልምድ ያላቸው መምህራን አማካይነት በቀጠይ አምስት ቀናት ስልጠና እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
በስልጠናው የክልሉ ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ እና የኤች አይቪ ጉዳዮች አስተባባሪ ወ/ሮ ስንታየሁ ማናዬ እንደገለጹት ሴት ተማሪዎች በትምህርት ያላቸውን ተሳትፎ ይበልጥ ለማጎልበት ጉልህ ጠቀሜታ እንዳሚኖረው ተናግረዋል።
