






አውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የ(LLRP )ፕሮጀክት በምዕራፍ አንድ ፕሮግራም በክልሉ የአርብቶ አደር አካባቢዎች ላይ ከትምህርት ቁሳቁስ አንስቶ እሰከ መሰረተ ልማት በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀው ለ5 ወረዳዎች ለተከታታይ አምስት ዓመታት የሚውል 17 ሚለዮን 136 ሺ 666.70 ዶላር ለፕሮጀክቱ ማሳኪያ መመደቡን ተናግረዋል። ይህ ትልቅ በጀት የተመደበለት ፕሮጀክት በውጤት እንድታጀብ የክልሉ ስትሪንግ ኮሚቴ ዕቅዱን ቆጥሮ ወስዶ ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ቦኒ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በምዕራፍ አንድ በ3 ወረዳዎች ባስመዘገበው ጠንካራ አፈፃፀም በምዕራፍ ሁለት ፕሮጀክቱ እንድቀጥል መደረጉን ተናግረው ከምዕራብ ኦሞ ዞን መኤኒት ጎልዲያ ፥መኤኒት ሻሻ ፥ሱሪና ማጂ እንዲሁም ከካፋ ዞን ጎባ ወረዳ ጨምሮ በድምሩ በአምስት የአርብቶ አደር ወረዳዎች ላይ በተለያዩ ዘርፎች ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
በአውደ ጥናቱ ላይ የ2017 በጀት አመት ዕቅድን ለተሳታፊዎች ያቀረቡት የክልሉ ቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ደረጀ በቀለ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት በሶስት ቴክኒካዊና ርስ በእርሱ በሚዛመዱ የስራ ዘርፎች ማለትም በተቀናጀ የሬንጅላንድ አስተዳደር የስራ ዘርፍ ፥የአየር ንብረት ተጽዕኖ መቋቋምና ዘላቂ የአርብቶ አደሩ ኑሮ ማሻሻል የስራ ዘርፍ የተዋቀረ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨረሻም በአውደ ጥናቱ በተሳተፉ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላትና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ሃሳብ አስተያየት ተሰጥቶበት የቀረበው የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በማጽደቅ አውደ ጥናቱ ተጠቋል ።
በዉቢት ደበበ
