የሚዲያ ባለሙያዎች በሚዛን አማን ከተማ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮው ባዘጋጀው የሚዲያ ቱር እየተሳተፉ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እና አመራሮች በሚዛን አማን ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።

በከተማው አማን ቀበሌ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሀ-ግብር ከሚዲያ ቱር ተሳታፊዎች በተጨማሪ መቀመጫቸውን ሚዛን ከተማ ያደረጉ ክልላዊና ሀገር-አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ባለሙያችና አጠቃላይ ሠራተኞች እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ተገኝተዋል።

የከተማው ካንቲባ ሰለሞን ሌዊ በዚህ ወቅት እንደገለፁት፥ ለክረምት ወራት ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ተከላ በከተማው በቂ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ቅድመ ዝግጅትን በሚመለከት ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡት የከተማ አስተዳደሩ የግብርናና አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስራቅ አስናቄ በመርሃ-ግብሩ ከ250ሺህ በላይ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጸዋል።

ለተከላው የሚኾን የቦታ እና የሰው ሀይል ልየታ፣ የጉድጓድ ቁፋሮ እንዲሁም የችግኝ ዝግጅት በተከማ አስተዳደሩ መከናወኑን በመጥቀስ በዕለቱ የከተማው ነዋሪ በነቂስ በመውጣት አሻራውን እንዲሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የሚዲያ ቱር ዓላማው ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በክልሉ እየተከናወኑ ባሉት የልማት ሥራዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መኾኑን የጠቆሙት የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ ከዚህ ተግባር ጎን ለጎን አረንጓዴ አሻራ ማኖራቸው በሀገራዊ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያሳድግ እንደሆነ ተናግረዋል።

የደቡብ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚዛን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ትዕዛዙ ኬንጫ በበኩላቸው፥ የችግኝ ተከላው ለአከባቢው ዘርፍ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መኾኑን በመግለጽ በየጊዜው ከሚከናወነው ትከላ ባሻገር የተተከሉትን እንክብካቤና ጥበቃ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በችግኝ ተከላዉ የተሳተፉት ጋዜጠኞች ከአሁን ቀደም በአረንጓዴ አሻራ ተከላ ወቅት ዘገባ ላይ ትኩረት ስለሚናደርግ አሻራችንን ብዙም እያሳረፍን አልነበርንም፤አሁን በራሳችን ነገ ከሚጀመረዉ ክልላዊ ተከላ ቀደመን አሻራችንነ ማኖራችን አስድስቶናል ስሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ች የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ፣የሚዛን አማን ከተማ አመራሮች ፣የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች እና የሚዲያ ቱር አባላት ተሳትፈዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *