


ኢትዮጵያ በደን ዘርፍ ከልማት አጋሮች የምታገኘውን ድጋፍና ጥቅም ለማሳደግ የሚያስችል የአረንጓዴ ዐሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ፀደቀ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባ÷ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አሥተዳደር አዋጅን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት አዋጁን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት÷ ዘላቂ ፈንድ ከማቋቋም አንጻርና ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ጥረት ጥሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የሀገር ውስጥን አቅም አሟጥጦ ለመጠቀምና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአየር ንብረት ለውጥ የሚደረጉ ድጋፎችን ለማግኘት የሚያስችል አዋጅ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል፡፡
