የክልሉ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 47ኛ መደበኛ ስብሰባዉን በሃለላ ኬላ አካሂዷል።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት

መስተዳድ ምክር ቤት ዛሬ በሃላላ ኬላ ባካሄደዉ 47ኛዉ መደበኛ ስብሰባ በ1ኛ አጀንዳነት የተመለከተዉ የክልሉ መንግስት የአስፈጻሚ ተቋማት የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ በመሉ ድምጽ አጽድቋል።

ምክር ቤቱ በ2ኛ አጀንዳነት የመንግስት ፍርድ ቤቶች የዳኝነት አገልግሎት ለመወሰን የወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ አስተያየት በመስጠት ወደ ምክር ቤቱ መርቶታል።

ምክር ቤቱ በ3ኛ ደረጃ በተጨማሪ በጀትነት ለክልሉ ካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እንዲዉል የቀረበዉን 657 ሚሊየን 600 ሺህ ብር ላይ ተወያይቶ ተጨማሪ በጀት ሆኖ እንዲጸድቅ በሙሉ ድምጽ በመወሰን ለምክር ቤቱ መርቶታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *