




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ገቢዎች ቢሮ ለአንድ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ያስገነባውን የመኖሪያ ቤት ርክብክብ አድርገዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ አስተዳደር ህብረት ቀበሌ በልዩ ስሙ ዶሮ እርባታ መንደር ለሚገኙት ወ/ሮ ተዋበች ዱባለ ያስገነባውን ቤት ዛሬ ርክክብ አድርጓል።
በክልሉ በሚገኙ ተቋማት አማካኝነት ለአቅመ ደካሞችና ለአረጋዊያን ቤት ገንብቶ መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በርክብክቡ ወቅት የተገኙት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ እንደ የብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር በሆኑት ፕሮግራሞቹ አቅመ ደካሞችንና አረጋውያንን እንዲሁም በዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ የሚገኙ ወገኖችን የመደገፍ ተግባር በትኩረት እየተሰራበት እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ህይወት አክለውም በግንባታው ሂደት ተሳታፊ የነበሩ የቴፒ ከተማ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ባልደረቦችን የህብረት ቀበሌ አመራርና ማህበረሰብን እንዲሁም ግንባታውን የፈፀመው ቅዱስ ግንባታ ማህበር ላሳዩት የመደጋገፍና የመተባበር ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።
በሀገራችን ብልፅግና እውን ሆኖ ዜጎቻችን የተሻለና ኑሮ እንዲኖሩ ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ ለልማት ማዋል እንደሚያስፈልግ የገለፁት ኃላፊዋ ሁሉም ዜጋ የግብር ጉዳይ የኔም ጉዳይ ነው ብሎ እንዲሠራና በግብይት ወቅት ደረሠኝ ጠይቆ በመቀበልም የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልክት አስተላልፈዋል።
ቤት ተገንብቶ የተሰጣቸው አረጋዊ ወ/ሮ ተዋበች ዱባለ በሚያፈስ ደሳሳ ጎጆ በደጋፊ እጦት ችግር ውስጥ እንደነበሩ በመግለፅ አሁን ቢሮው መኖሪያ ቤት ገንብቶ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።
