ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ህብረ ብሔራዊ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ማድረግ ይገባል ። አቶ መቱ አኩ

Spread the love

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ በቴፒ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው ።

“ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሔራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ባለው የማጠቃለያ መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ ክልላዊ እና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ህብረ ብሔራዊ አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በዓሉን በምናከብርበት ወቅት ሀገራዊ መግባባትና ህብረብሔራዊ አንድነታችንን በምናጠናክርበት ጉዳዮች ዙሪያ ያሉ ችግሮችና የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ጥልቅ ውይይት ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉም ተናግረዋል።

የተከበሩ አቶ መኩ 19 ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ስናከብር አስተሳሰቦቻችን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል ።

የጋራ እሴቶቻችንን ለህብረብሔራዊ አንድነት፣ ሀገራዊ ውይይትና ምክክር ለዘላቂ ሰላም፣የህግ የበላይነት መከበር ለዘላቂ ሰላም መሠረት ነው የሚሉ በዋናነት የዕለቱ መልዕክት መሆናቸዉንም አቶ መቱ በንግግራቸው አንስተዋል።

የማጠቃለያው መድረክ የህገ_መንግስት እና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ስራዎችን የሚያተኩሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ።

በዕለቱም የክልሉ የኪነት ቡድን ባህላዊ ጭፈራዎች እና የፖሊስ አባላት ትዕይንት ለበዓሉ ድምቀት የተከናወኑ ሁነቶች ሲሆኑ የፓናል ውይይት የጥያቄና መልስ ውድድር በማድረግ በዓሉ እንደሚጠናቀቅ ከወጣው የድርጊት መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *