
በፓርቲያችን ብልጽግና አሻጋሪ እሳቤዎች በመመራት በክልሉ ተጨበጭ ውጤቶች እየተመዘገበ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መንግስቱ መኩሪያ ገለጹ።
የቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መንግስቱ መኩሪያ በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2016 ዕቅድ አፈጻጸምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
የክልሉ ህዝብ በሀገራዊ ለዉጥ እና በመንግስት የሪፎሪም ፕሮግራሞች ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ በመሆኑ በክልሉ ተጨባጭ ውጤቶች እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።
የፓርቲያችን መርሆች ፣እሴቶች እና እሳቤዎች እንደ ክልል ለጀመርነው ተስፋ ሰጪ የለውጥ ሂደት እና ለተገኘው ስኬቶች አይተኬ ሚና እየፈጠሩ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትልሞቻችን አቅም መሆን የሚችሉ መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው በአግባቡ መተግበር ስንችልም ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የማሸጋገር አቅም እንዳላቸው ገልጸዋል።
የፖለቲካ ንቅናቄ ናየአደረጃጀት ስራዎች በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ በመቀጠላቸዉ የህዝቡ ከዚህ በፊት የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሆኑት የጤና፣የንፁህ መጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት፣መንገድና ድልድዮችን ደረጃ በደረጃ ማነቆዎች እየተፈቱ ይገኛሉ ሲሉ ገልጸዋል።
ሀገራዊና ክልላዊ የልማት አጀንዳዎች ላይ ህዝቡ ከፓርቲያችን ብልጽግናና ከመንግስት ጎን በመቆም የሠላምና ፀጥታ ሥራ፣ የት/ቤቶች ደረጃ ማሻሻልና ግብአት የማሟላት ስራ፣ አረንጓዴ አሻራ፣ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወይም ሰው ተኮር ተግባራት መሰል…ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
ለዚሁ ስኬት በየደረጃው ያለው ፓርቲውን የሚያጠናክሩ ከአንዱ የተግባር ምዕራፍ ወደ ሌላው ሲሸጋገሩ በተግባር እየጠናከሩ የመጡ የህዋስ አደረጃጀት መኖራቸው የገለጹት ኃላፊው በቀጣይ የፓርቲውን እሳቤ በመረዳት ለሀገር ብልጽግና በቁርጠኝነትና በመሰጠት ህዝቡን ከልብ የሚያገለግሉ ጥራት ያለውን አባል በመፍራት የብልጽግና እሳቤዎችን ከዳር ለማድረስ በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ እደሚሰራ ኃላፊ አብራርተዋል።
የግማሽ ምርጫ ዘመን አፈፃፀማችን በውጫዊና በውስጣዊ ፈተናዎች እየተፈተነም ጭምር አያሌ ስኬቶችን ለማስመዝገብ ተችሏል ። በቀሪዎቹ ሁለት ተኩል ዓመታት አዳዲስ ድሎችና ስኬቶች ማስመዝገብ ብቻ ሳይሆን ባለፉት ጥቂት ዓመታት በፈተና ብዛት ያመለጡንን ዕድሎች በሚያካክስ መንገድ ከሰራን ምንዳችንን ለማብዛት በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች በተላይም በልማት አጀንዳዎችና ሠላማን ከማጽናት ረገድ ተቀራርቦ በመስራትና ጤናማ ግንኙነት በመፍጠር የትብብርና የፉክክር ሚዛንን ጠብቆ በመስራት የዴሞክራሲ ባህል በመገንባት በሀሳብ የበላይነትና በትብብር መንፈስ ከመስራት አንፃር የተጀመሩ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸውም በመግለጫቸው አጽዕኖት አብራርቷዋል።
የሴቶችንና የወጣቱን ኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል በርካታ ተግባራት መከናወኑን የገለጹ አቶ መንግስት በክልሉ እየተተገበረ በሚገኘው የበጎ ፍቃድ አገልግሎትም ሆነ ሌሎች ልማቶች ላይ የመሪነት ሚናቸውን በመወጣት ደማቅ አሻራቸውን በማኖር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
ከጊዜ ወደ ጊዜ የአንድነትና የወንድማማችነት ስሜት እያደገ መምጣቱን የገለጹት ኃላፊው ከአጎራባች ክልሎችና በክልሉ ባሉ ዞኖች በተደረገዉ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የእርስበእርስ መረዳዳት፣
መደጋገፍና መተጋገዝ ማህበራዊ መስተጋብር እየተጠናከረ መምጣቱንም ገልጸዋል።
በዚህም ካለን እምቅ አቅምና እርስ በርስ ከመረዳዳት አኩሪ ታሪክና ምቹ ሁኔታ አንፃር ያልተጠቀምንባቸውን ማህበራዊ ድልብ አቅማችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ በመጠቀም እያጋጠመን ያለውን ፈተና ወደ ዕድል መቀየርን የቀጣይ ትኩረት አድርገን መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡
ፓርቲያችን ብልጽግና ከሀገራችን ፖለቲካዊ ስብራቶች ከወረሳቸው ዕዳዎች ዋነኛው ገዢ ሀገራዊ ትርክት አለመገንባቱ እንደሆነ ኃላፊው በመግለጫቸው ያብራሩ ሲሆን መላው አመራር እና አባል ብሔራዊነትን በጠንካራ ዐርበኝነት ላይ በመመስረት ገዢ ሀገራዊ ትርክት ለመገንባት የመሪነት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ከፋፋይ ትርክት የወደቅንባቸው አክሳሪ በመሆኑ ራሳችንን እና ሀገራችንን ከአፍራሽ ትርክት በመጠበቅ የተሻለ ምንዳ ያላትን ሀገር ለቀጣይ ትውልድ ለማስረከብ መላው አባል እና አመራር በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በክልሉ ያሉትን እምቅ ሀብትና ፀጋዎችን በአግባቡ አስተባብሮና አቀናጅቶ በመጠቀም ከተረጂነት አስተሳሰብና ድርጊት ለማለቀቅ በቀጣይ ግለቱን የጠበቀ ውጤታማ የህዝብ ንቅናቄ እንደሚኖር ገልጸው ለተግባራዊነቱም ሁሉም የድርሻውን መወጣት መቻል አለበት ሲሉ አስገንዝበዋል።
ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማረጋገጥ በህዝቦች መካከል ልዩነት የሚያመጡ ጉዳዮችን በሀሰብ የበላይነት ፣በተሟላ ውይይትና መግባባት በመመከት ገዢ፣አካታችና አሰባሳቢ ትርክት ላይ በማተኮር መስራት የመገናኛ ብዙሃንና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና አመራር ትልቅ ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዚህም እንደ ተቋምም ሆነ አንደ አመራርና አባል ዘመኑን በዋጀ መልኩ የድህረ- እውነት የመረጃ ዘመን በመረዳት በእውነትና በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ማህበራዊ ሚዲያን እና ብዙኃን መገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም ብሔራዊነት ገዢ የትርክት እንዲሰርጽና የሀሳብ የበላይነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት መስራት ይገባናል ብለዋል።
የፓርቲው አመራርና አባልን የፖለቲካ አቅም ለመገንባት የተሰጠው የአቅም መገንቢያ ስልጠና በብልፅግና እሳቤዎችና መርሆዎች ላይ ወጥ አረዳድና የሀሳብ ጥራት ለመፍጠር ፣የአስተሳሰብና የተግባር መቀራረብን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች በውጤት የሚለካ ለውጦች እየተመዘገቡ ቢሆንም የብልጽግና ራዕንና ዓላማን በተሟላ ሁኔታ ከማረጋገጥ አኳያ ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ አቶ መንግስቱ ገልጸዋል።
ስልጠናው የፓርቲውን ዓለማ ፣መርሆዎችና እሴቶችን ተረድቶ ተልዕኮውን በሚገባ እንዲወጡ ከመስቻሉም ባሻገር የፓርቲያችንን የልማት አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ በተለይም በበጋ ስንዴ ልማት፣በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ፣በገቢ አፈጻጸም አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ ችሏል።
የአረንጓዴ አሻራ ስራዎቻችን አጠናክረን በመቀጠል ዘለቂና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወኑን ገልጸው ከተሞች የብልጽግና ማዕከል እንዲሆኑንና የከተሞች ልማትን ከገጠር አካባቢዎች ልማት ጋር ተመጋጋቢ እንዲሆኑ በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ፣በሌብነትና ብልሹ አሠራር በቀጣይ በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ ንቅናቄ በመፍጠር በፓርቲያች ሰው ተኮር ባህሪ የህዝቡ እርካታ የመጨመር ተግባር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰዋ ል።
በመጨረሻም በ2016 ዓ.ም በጥንካሬ የታዩ ተግባራትን በማላቅና በድክመት የተገመገሙ ተግባራትን ከላይ እስከ ታች አደረጃጀቶቻችን እና አባሎቻችንን በማነቃነቅ ፣ ድጋፋዊ ሱፐርቭዥን ፣የኢንስፔክሽን ስራ፣የአፈፃፀም ግምገማ ፣የመስክ ምልከታና ግምገማና የውሰጠ -ፓርቲ ዴሞክራሲ በማጠናከር ለተግባር ውጤታማነት ተግተን እንሰራለን ብለዋል።
