




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አዘጋጅነት ”ሥነ-ምግባራዊ አመራር ለተቋም ግንባታ እና የሙስና መከላከል ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለጉራፈርዳ ወረዳ እና ለቢፍቱ ከተማ አስተዳደር አመራሮችናየመንግስተ3 ሠራተኞች በቢፍቱ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚነሸር ሙሉሰው ዘውዴ እንደተናገሩት የሙስና ተጽዕኖ ስልጣንን አለአግባብ ከመጠቀም በላይ መሆኑን ተናግረዋል ።
ሙስና የህዝብ እምነት ክህደት መሆኑን የገለጹት ኮሚሽነሩ ተቋማትን በማዳከም ግብዓትን ከወሳኝ አገልግሎቶች ያስወጣል ብለው የህዝባችንንም የልማት ምኞትና ተስፋ እነደሚያዳክም ገልጸዋል።
በግዢ ማጭበርበር ምክንያት የጤና ተቋማት የመድሐኒት እጥረት ስገጥማቸው የሚጎዱት ደሆች መሆናቸውን የገለጹት ኮሚሽነር ሙሉሰው በአድሏዊ አሠራር ወጣቶችም የዚህ ሰላባ ተጎጂዎች ናቸው ብለዋል።
ሙስናን በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ ያነሱት ኃላፊዉ ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ ማቆምን ተልዕኮ ሰንቆ ኮሚሽኑ እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።
አያያዘውም በወረዳው የሙስና ተጋላጭ የሥራ ክፍሎችን በመለየት ግንዛቤ መፍጠር ወሳኝ በመሆኑና በሁሉም የመንግስት እርከኖች የታማኝነት ባህል መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናውን ለመስጠት ተገድደናል ብለዋል።
ሠልጣኞች በማህበረሰቡ ውስጥ የመንግስት ዓይን እና ጆሮ በመሆን በሁሉም ዘርፍ ህዝቡን ከሙስና ተጽዕኖ ለመከላከል ግንባር ቀደም ሊትሆኑ ይገባል ብለዋል።
ከስራ ሥነ-ምግባር ጋር ተያይዞ የኮምሽኑ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አቶ በፍቃዱ ዘለቀ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
