የክልሉን የግብርና ምርታማነት ማነቆዎችን ለመፍታት እንዲቻል በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ ውጤታማ የምርምር ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ተገለጸ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተጠናቀቁ የግብርና ምርምር ተግባራት ሳይንሳዊ ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ዓለሙ ባደረጉት ንግግር ፣ኢንስቲትዩቱ የክልሉን የግብርና ምርትና ምርታማነት ማነቆዎችን ለመፍታት እና የግብርና ዘርፍ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በምርምር ዘርፉ የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ነው ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ የተጣለበትን ተልዕኮ ለመወጣት በሰብል ልማት፣በእንሰሳት እርባታ ፣በተፈጥሮ ሀብት እና በግብርና ኢኮኖሚክስ የተሰሩ የምርምር ተግባራትን በማከናወን ለተሻለ ውጤት በየጊዜው ጠንካራ ግምገማ እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።

የዛሬው መድረክ እስካሁን የተሰሩ የምርምር ተግባራት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ተጣርቶ ወደ አርሶ አደሩ እንዲደርሱ ለማድረግ በተመራማሪዎች እና በዘርፉ ሙያተኞች ለማስገምገም ያለመ እንደሆነም አስታውቀዋል።

በዚህም በተከታታይ ሁለት ቀናት 60 የምርምር ተግባራት የሚገመገሙ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በዛሬው ዕለት በክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተጠናቀቁ 16 የግብርና ምርምር ተግባራት ሳይንሳዊ ግምገማ እንደሚደረግም ገልጸዋል።

በመድረኩ ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ፣ከሀዋሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ፣ከጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ከጅማ ግብርና ምርምር ማዕከል፣ ከሲዳማ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እና ከቦንጋና ተርጫ የግብርና ምርምር ተቋማት የተውጣጡ ተመራማሪዎች ፣የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *