ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሳተፋሉ

Spread the love

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ አለ፡፡

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 14 መርሐ ግብሮች እንዳሉት በሚኒስቴሩ የወጣቶች ብሔራዊ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፋፊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዐቢይ ኃ/መለኮት ተናግረዋል።

የዳበረ የመደጋገፍ ዕሴትን ለማሳደግ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የላቀ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎን በማሳደግ አሠራሩን መዋቅራዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *