





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ከዛሬ ጀምሮ የሚሰጠውን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር አዲስ ፋና ትምህርት ቤት ተገኝተው አስጀምረዋል።
በክልሉ ከ1ሺህ 86 በላይ የማስተፈኛ ጣቢያዎች መካከል ከ38 ሺህ 5 መቶ 93 በላይ ተማሪዎች በሰባት የትምህርት ዓይነቶች ፈተናውን እየተፈተኑ ይገኛሉ።
በቀጣይም ከ48 ሺህ በላይ የ6 ክፍል ተማሪዎች በ5 የትምህርት ዓይነቶች እንደሚፈተኑም አቶ አልማዉ ገልጸዋል።
ፈተናዉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች እየተሰጠ ይገኛል።
